ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ
     
 
Banner


ቦርዱ 5ኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ በብቃት ማካሄዱን አስታወቀ

 

የምክር ቤቱ አባላትም ቦርዱ ላከናወናቸዉ ተግባራት አድናቆታቸዉን ገልፀዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገመንግሥት አንቀጽ 102 እና በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. መሠረት የተቋቋመ እንደመሆኑ ግዙፍ ሕዝባዊና ሕገመንግሥታዊ ኃላፊነት ተሸክሞ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ 5ኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ በብቃት ማካሄዱን ቦርዱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበዉ ሪፖርት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ2ዐዐ3 - 2ዐዐ7 ዓ.ም. የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ነድፎ ተንቀሳቅሷል ያሉት በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ቁልፍ እና አበይት ተግባራትን በመለየት የማስፈፀም አቅም ግንባታ እንደ ቁልፍ ተግባር ይዞ ለተለያዩ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ ለወጣቶች፣ ሴቶች፣ መምሕራን ማኅበራት፣ ለምርጫ ታዛቢዎች፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እና አባላት፣ ለምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ ለፍትሕ አካላት ሥልጠና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ከአበይት ተግባራት ውስጥ አንዱ የ2ዐዐ7 ጠቅላላ ምርጫ ለማስፈፀም የሚረዱ ዝግጅቶች ቀደም ብሎ በመጀመር ሥራዎቹን በቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ እለትና ድኅረ ምርጫ በመከፋፈል የምርጫው ሂደት ሁሉ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በተለይ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በመግባባትና በመወያየት መርህ መሠረት በማድረግ የፖለቲካ ምኅዳሩን በማስፋት ረገድ በርካታ ሥራ መሰራቱን የገለፁት የቦርዱ ሰብሳቢ የምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱ በአዲስ መልክ ተደራጅተዉ በአጠቃላይ የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ በወቅቱ ተዘጋጅቶ ተግባር ላይ መዋሉን ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መርጋ ለምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በወቅቱ ተደራጅተዉ መሰራጨታቸዉን ገልጸዉ የመራጮችና የዕጩዎች ምዝገባ በታቀደለት መሰረት መፈፀሙንና መራጩና ተመራጩ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡ በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ በህጉ መሰረት ፈጣን መልስ ተሰጥቷል ያሉት የቦርዱ ሰብሳቢ በምርጫ ዕለት መራጩ ሕዝብ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በየተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ በመገኘት በተረጋጋ ሁኔታ ድምጹን እስከ ምሽቱ 12፡ዐዐ ሰዓት የሰጠ ከመሆኑም ባሻገር ምርጫዉ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ እና ተዓማኒ ሆኖ ተጠናቋል፡፡ የጊዜያዊና የመጨረሻ ዉጤት በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለሕዝቡ ይፋ ተደርጓል ነዉ ያሉት፡፡

ከምክር ቤቱ አበላታ መካከል የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸዉ ምርጫዉ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ቦርዱ ዓይነተኛ ሚና መጫወቱን ገልፀዉ ካመሰገኑ በኋላ በምርጫዉ ሕዝብ ለሰጠዉ ድምጽ ተገዥ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት መስተካከል ይኖርባቸዋል ሲሉ በምርጫዉ ሂደት ላይ ያጋጠሙ ጥቃቅን ችግሮችን ከጠቆሙ በኋላ እንደ አጠቃላይ ቦርዱ ያከናወናቸዉን ተግባራት አድንቀዋል፡፡


 


የጊምቦ ጋዋታ የምርጫ ክልል ዉጤት በቦርዱ ዉሳኔ አገኘ

 

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በካፋ ዞን በጊምቦጋዋታ የምርጫ ክልል በቦርዱ የይራዘም ዉሳኔ ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተካሄዶ የነበረዉ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁንና ዉጤቱም ቦርዱ በግል ዕጩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የቀረበዉን አቤቱታ ከተመለከተ በኋላ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አጠቃላይ ዉጤት ይፋ በተደረገበት ወቅት መገለፁ ይታወቃል ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጊምቦ ጋዋታ ምርጫ ክልል ግንቦት 16/2007 . ሊካሔድ የነበረዉ ምርጫ በቅስቀሳ ወቅት አጋጥሞ በነበረዉ ችግር የተነሳ ለሰኔ 7/2007 . እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል፡፡በዚህም መሰረት ሰኔ 7/2007 . 98 የምርጫ ጣቢያዎች በተካሄደዉ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ 55,645 ህዘብ በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ላይተሳትፏል፡፡
የድምጽ አሰጣጥ ስርዓቱ ሰላማዊ፣ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተካሄደ ከመሆኑም በላይ ለመራጭነት ከተመዘገበዉ ህዝብ ዉስጥ ድምጽ የሰጠዉ 98 በመቶ የሚያህለዉ ነበር፡፡ ይሁንና በምርጫ ክልሉ በግል በዕጩነት የቀረቡት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የተለያዩ በደሎች ተፈጽመዉብኛል በሚል አቤቱታ በማቅረባቸዉ ቦርዱ ሁኔታዉን መርምሮ ዉሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም የጊምቦ ጋዋታ ምርጫ ክልል ብቻ ሳይገለጽ መቅረቱ ይታወሳል፡፡

ቦርዱ ሰኔ 19 እና ሰኔ 21 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደዉ ስብሰባ ሁኔታዉን በጥልቀት በመመርመር የግል ዕጩዉ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት እንደሌለዉ ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡ ግለሰቡ ያቀረቡት አቤቱታ በተሻሻለዉ የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም መሰረት በየደረጃዉ ለሚገኙ የምርጫ ጽ/ቤቶች ቅሬታ ሰሚ አካላት ቀርቦ የታየና ዉሳኔ የተሰጠበት ባለመሆኑ ቦርዱ በቀጥታ ተቀብሎ የሚያይበት የህግ መሰረት የሌለ ከመሆኑም ባሻገር ጉዳዩ ሲመረመር የቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ አልተገኘም ሲል ወስኗል፡፡

ቦርዱ ጨምሮ እንደገለፀዉም በጊምቦ ጋዋታ ምርጫ ክልል ሰኔ 7/2007 ዓ.ም የተካሄደዉ ምርጫ ምንም ዓይነት የህግም ሆነ የአሰራር ግድፈት ያለተፈጸመበት መሆኑን በማረጋገጥ አቤቱታዉ ተቀባይነት እንደሌለዉ ገልጻል፡፡ በዚህም መሰረት የደኢህዴን /ኢህአዴግ ዕጩ የሆኑት ዶ/ር መብራህቱ ገ/ማርያም ካሎ 44,035፤ በግል ዕጩነት የቀረቡት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ 9,911፤ከመድረክ በዕጩነት የቀረቡት አቶ አባቢ ዙረጋ ገ/ማርያም 788፤ከቅንጅት የቀረቡት አቶ አለሙ አድነዉ ጋዋ 558፤ ከኢዴፓ የቀረቡት መቶ አለቃ አድማሱ ገ/ስላሴ 179፤ከኢራፓ የቀረቡት አቶ ፍሬዉ አደቶ ገ/ማርያም 93፤ ከመኢአድ የቀረቡት አቶ አክሊሉ አለማየሁ ገብሬ 81 ድምጽ ያገኙ ሲሆን የደኢህዴን /ኢህአዴግ ዕጩ የሆኑት ዶ/ር  መብራህቱ ገ/ማርያም አሸናፊ ሆነዋል ፡ ለክልል ምክር ቤት በተካሄደዉ ዉድድርም ደኢህዴን /ኢህአዴግ ያቀረባቸዉ ዕጩዎች አሸንፈዋል፡፡

ግንቦት 16 በተካሄደዉ የድምጽ አሰጣጥ ላይ ድምጹን ለሰጠዉ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንገልጸዉ እንደነበርነዉ ሁሉ የጊምቦ ጋዋታ ሕዝብም በምርጫዉ ሂደት ላይ ላሳየዉ ጨዋነት የተመላበት ተሳትፎ ያለንን የላቀ ክብር ልንገልጽ እንወዳለን፡፡

 


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

 

2007 ዓ/ም ጠቅላላ ምርጫ

አጠቃላይ ውጤት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ/ም በመላው ሀገራችን የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ለማስፈጸም ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመመካከር ባፀደቀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫው ነፃ፣ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ አስፈፅሟል፡፡

በተሸሻላ የኢትዮጵያ ምርጫ አዋጅ ቁጥር 532/99 አንቀጽ 77 መሰረት የምርጫ ሂደት ከተጠናቀቀ እና አስፈላጊ መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ቦርዱ ይፋ  ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ነጥቦች የያዘ ይፋዊ መግለጫ ያወጣው ብሎ ደንግጓል፡፡

· የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር

· ድምጽ የሰጡ መራጮች ቁጥር

· ድምጽ የሰጡና ያልሰጡ ተመዝጋቢዎች መጠን በመቶኛ

· የአሸናፊ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስምና ለየምክርቤቱ ያሸነፉትን መቀመጫ ብዛት

· ጥቅም ላይ የዋለ፣ዋጋ ያለው እና ዋጋ አልባ የድምጽ መስጫ ወረቀት

ቦርዱ ሰኔ 11 ቀን 2007 ዓ/ም በአካሄደው 010/07 መደበኛ ስብሰባው ከየምርጫ ክልሎች ለቦርዱ የደረሰውን የምርጫ ውጤት ቅሬታ ቀርቦበት ውሳኔ ያላገኘ አቤቱታ አለመኖሩን መርምሮ በማረጋገጥ በጊዜ ሰሌዳው መሠረት እነሆ ዛሬ የምርጫውን ውጤት በይፋ ለህዝብ ለመግለጽ ቀርቧል፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት በተሻሻለው ምርጫ አዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 77 መሰረት ቦርዱ የምርጫውን አጠቃላይ ውጤት ከዚህ እንደሚከተለው ይፋ ያደርጋል፡፡

1. በመራጭነት  የተመዘገበ ህዝብ

ü ወንድ 19,076,625 (51.6%)

ü ሴት 17,774,863 (48.4%)

ü በጠቅላላ 36,851,461(100%)

መራጭ ሕዝብ ተመዝግቧል፡፡

2. በምርጫው የተወዳደሩ ፓርቲዎች ብዛት................. 58

3. የፖለቲካ ፓርቲ እና ግል እጩዎች ብዛት

ሀ. ተወካዮች ምክርቤት ................... 1828

ወንድ......................... 1527 (87.6%)

ሴት ........................  301 (12.4%)

ለ. ለክልል ምክርቤቶች 3991 እጩዎችን

ወንድ ........................... 3022 (84.7%)

ሴት............................. 969 (15.3%)

በተጨማሪ በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 9 እና ለክልል ምክርቤቶች 3 በድምሩ 12 ወንድ እጩዎች ተመዝግቧል፡፡

4. የጠቅላላ ምርጫ ውጤት

ሀ. ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 547 መቀመጫዎች አሉት፡፡  በጠቅላላ 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 9 የግል እጩዎች በ547ዎቹ ላይ ተወዳድሯል፡፡ ከነኝህ ውስጥ ኢህአዴግ በ 5 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች በድምሩ በ 500 ወንበሮች ላይ  ማለትም፡-

ü በትግራይ...........................   በ38 ምርጫ ክልሎች

ü በአማራ..............................  በ137 ምርጫ ክልሎች

ü በኦሮሚያ............................. በ178 ምርጫ ክልሎች

ü በደቡብ/ብ/ብ/ህዝቦች...............በ 122 ምርጫ ክልሎች

ü በሐረሪ ...............................በ 1 ምርጫ ክልል

ü በአዲስ አበባ ........................በ 23 ምርጫ ክልሎች

ü በድሬዳዋ ..............................በ 1 ምርጫ ክልል

ተወዳድሮ ዋጋ ካለው 33201969 ድምጽ ውስጥ 27,347,332 (82.4%) ድምጽ በማግኘት በሁሉም አሸንፏል፡፡  ካሸነፉት እጩዎች መካከል 212 ወይም 38.8 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡

ማስታወሻ፡- በደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል የጊምቦ ገዋታ ምርጫ ክልል ውጤት አልተካተተም፡፡

በቀሪዎቹ 46 መቀመጫዎች ደግሞ፡-

ü አብዴፓ...............................በ 8 ምርጫ ክልሎች

ü ኢሶህዴፓ.............................በ 24 ምርጫ ክልሎች

ü ቤጉህዴፓ...............................በ 9 ምርጫ ክልሎች

ü ጋህዴን.................................በ 3 ምርጫ ክልሎች

ü ሐብሊ..................................በ 1 ምርጫ ክልል

ü አሕዴድ ..............................በ 1 ምርጫ ክልል አሸንፈዋል፡፡

ለ. ለክልል ምክርቤቶች

የክልል ምክርቤቶች መቀመጫ ብዛት የሚወሰነው በያንዳንዱ ብሔራዊ ክልል መንግስት ነው፡፡  በዚህ መሰረት በያንዳንዱ ክልል የተወዳደሩት ፓርቲዎች፣ ያገኙት መቀመጫ እና  አሸናፊ ፓርቲ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

1. በትግራይ ክልል 6 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው ህወሓት/ኢህአዴግ 2,374574 (99.39%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 152 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


2. በአፋር ክልል 9 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው

· አብዴፓ 817,107 (99.8%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 93 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-

· አህዴድ  8253 (97.17%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው    3 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


3. በአማራ ክልል 13 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው ብአዴን/ኢህአዴግ 7,314564( 96.92%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 294 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


4. በኦሮሚያ ክልል 16 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው ኦህዴድ/ኢህአዴግ 10877190 (93.12%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 537 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


5. በኢ/ሶማሌ ክልል 6 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው  ኢሶህዴፓ 2621088 (99.97%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 273 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


6. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 5 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው ቤጉህዴፓ 222790 ( 81.03%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 99 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


7. በደ/ብ//ህ ክልል 21 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው ደኢህዴን/ኢህአዴግ 5,836,849 (93.74) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 345 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


8. በጋምቤላ ክልል 1 የፖለቲካ ፓርቲ ተወዳድሮ ጋህአዴን 195335 (100%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 155 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-


9. በሃረሪ ክልል 5 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳድረው

· ሐብሊ   19791(50%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 18 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-

· ኦህዴድ/ኢህአዴግ 84097 (50%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 18 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-

ለክልል ምክርቤቶች ካሸነፉት እጩዎች መካከል 800 ወይም 40.3 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡


ለብሔራዊ ክልል ምክርቤቶች ያሸነፉ ፓርቲዎች

ተ/ቁ

ክልል

የወንበር ብዛት

የተወዳዳሪ ፓርቲ ብዛት

ያገኙት ድምጽ

ያሸነፈው ወንበር

አሸናፊ የፖለቲካ ፓርቲ

1

ትግራይ

152

6

2,374574

152

ህወሓት/ኢህአዴግ

2

አፋር

96

9

817107

93

አብዴፓ

8253

3

አህዴድ

3

አማራ

294

13

7314564

294

ብአዴን/ኢህአዴግ

4

ኦሮሚያ

537

16

10877190

537

ኦህዴድ/ኢህአዴግ

5

ኢ/ሶማሌ

273

6

2621088

273

ኢሶህዴፓ

6

ቤ/ ጉመዝ

99

5

222790

99

ቤጉህዴፓ

7

ደ/ብ/ብ/ህዝቦች

348

21

5836849

345

ደኢህዴን/ኢህአዴግ

8

ጋምቤላ

155

1

195335

155

ጋሕአዴን

9

ሐረሪ

36

5

19791

18

ሐብሊ

84097

18

ኦህዴድ/ኢህአዴግማስታወሻ፡ በደቡብ ክልል ጊንቦ ገዋታ ምርጫ ክልል ውጤት አያካትትም


ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክርቤቶች አሸናፊ እጩዎች ብዛት በጾታ

 

ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት

ለክልል  ምክርቤት


አሸናፊ ፓርቲ

ወንድ

ሴት

ድምር

ሴት %

ወንድ

ሴት

ድምር

ሴት%

ህወሓት/ኢህአዴግ

24

14

38

36.8

75

77

152

50.7

ኢህአዴግ

14

9

23

39.1

0

0

0

0.0

አብዴፓ

6

2

8

25.0

76

17

93

18.3

አህዴድ

1

0

1

0.0

3

0

3

0.0

ብአዴን ኢህአዴግ

81

56

137

40.9

156

138

294

46.9

ኦህዴድ/ኢህአዴግ

117

63

180

35.0

298

257

555

46.3

ኢሶህዴፓ

10

14

24

58.3

136

50

186

26.9

ቤጉህዴፓ

5

4

9

44.4

80

19

99

19.2

ደኢህዴን/ ኢህአዴግ

73

49

122

40.2

181

163

344

47.4

ጋሕአዴን

3

0

3

0.0

111

44

155

28.4

ሐብሊ

0

1

1

100.0

10

8

18

44.4

ድምር

334

212

546

38.8

1126

773

1899

40.7


5. የድምጽ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም

ምርጫውን ለማስፈጸም ቦርዱ ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክርቤት ለያንዳንዳቸው 40,536,607 የድምጽ መስጫ ወረቀት የተላከ ሲሆን ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ድምጽ ከተሰጠበት የድምጽ መስጫ ወረቀት ውስጥ 3.3 ከመቶ ብቻ ዋጋ አልባ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ዝርዝሩ  እንደሚከተለው ቀርቧል

የመራጭ ዓይነት

የተላከ

ዋጋ ያለው

ዋጋ አልባ

ዋጋ አልባ(%)

የተበላሸ

የተረፈ

ድምር

40,536,607

33222801

1,130,329

3.30

520,379

5,663,098

 

prev
next

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

ቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ በማዉጣት የምርጫ እንቅስቃሴዉም በዚያዉ አግባብ እየተከናወነ ይገኛል፡፡...

ሙሉ ዜና

በዓሉ ቦርዱ የተጣለበትን ህገ መንግሥታዊ አደራ በላቀ ተነሳሽነት

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 5ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ የሚገኝበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ተልኮችንን በትጋት እንድንወጣ እና የተጣለብንን ህገ መንግሥታዊ አደራ በላቀ ተነሳሽነት እንድንፈጽም ስንቅ ይሆነናል ሲሉ የቦርዱ ም/ሰብሳቢ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮችና ሰራተኞች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በማ...

ሙሉ ዜና

የምርጫ ክልል ምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ፡

News image

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመላዉ ሀገሪቱ በተመረጡ 11 ከተሞች ሲሰጣቸዉ የነበሩ የምርጫ ክልል ምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና በስኬት አጠናቀቀ፡፡ ቦርዱ በጂግጂጋ ከተማ ባዘጋጀዉ የክልሉ ምርጫ አስፈጻሚዎች የመዝጊያ ስልጠና ላይ በተለይ የታዳጊ ክልሎችን የምርጫ ክልል ሽፋን ከማስፋት አንጻር ለምርጫዉ ሁሉን አቀፋዊነት ማሳካት የድርሻዉን እየተወጣ ስለመሆኑ እንደሚያሳይ በክልሉ የሚገኙ የምርጫ ክልል ...

ሙሉ ዜና
 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ