ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ መግለጫዎች
     
 
Banner

መግለጫዎች
የመራጮች እና የስነዜጋ ትምህርት በየክልሉ የሬዲዮ የመገናኛ ብዙኃን ከጥቅምት 1 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ጀምሮ መሠራጨቱን በተመለከተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ PDF Print E-mail


የመራጮች እና የስነዜጋ ትምህርት በየክልሉ የሬዲዮ የመገናኛ ብዙኃን ከጥቅምት 1 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ጀምሮ መሠራጨቱን በተመለከተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

 

በተሻሻለው የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. አንቀጽ 89 እንደተደነገገው፤

-     ቦርዱ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም መራጩ ስለምርጫው በቂ ግንዛቤ የሚያገኝበት ስልት በመቀየስ የመራጮች እና የስነዜጋ ትምህርት ይሰጣል፣

 

-     ቦርዱ የመራጮች እና የስነዜጋ ትምህርት በሌላ ድርጅት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የማስተማር ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፣

 

-     ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አግባብ ካለው አካል ጋር በመዋዋል የመራጮችና የስነዜጋ ትምህርት እንዲሰጥ ሊያደርግ ይችላል፡፡

 

በዚሁ መሠረት ቦርዱ ቀደም ባሉ ምርጫዎች ሲሰጥ የነበረው የመራጮችና የስነዜጋ ትምህርት ወጥነት እና ተከታታይነት የሌለው እንደነበር በማረጋገጥ ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የማስተማሪያ ሰነድ አዘጋጅቶ በ2ዐዐ2 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ሰነዱ በወቅቱ ቦርዱ ባዘጋጃቸው የተለያዩ አውደጥናቶች ላይ በመስኩ ባለሙያዎች በጥልቀትና በስፋት ተገምግሟል፡፡ በመሆኑም ጥሩ ግብአት አግኝቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ቦርዱ በ2ዐዐ2 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የማስተማሪያ ሰነዱ በመገናኛ ብዙኃንና በተለያዩ የትምህርት መስጫ ዘዴዎች ለመራጩ ሕዝብ ተገቢውን የምርጫ አፈፃፀም መረጃ እንዲደረስ አድርጓል፡፡ ስለሆነም ሰነዱ ለምርጫው ስኬታማነት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ቦርዱ በ2ዐዐ2 ዓ.ም. የሰነዱ ትግበራ ላይ ያገኛቸውን ተሞክሮዎችን፣ በሀገር ውስጥ እና በውጪ አውደ ጥናቶች ላይ በተለያዩ ጊዜያት የቀሰማቸውን ልምዶችና ተሞክሮዎች፣  ከበርካታ ተቋማትና ባለሙያዎች በቂ ግብዓት ከአገኘ በኋላ ሰነዱን ወደ ማኑዋል/መጽሐፍ ለውጦታል፡፡

ማኑዋሉ በአማርኛ  እና በተለያዩ የክልል የሥራ ቋንቋዎች ማለትም በትግርኛ፣ በአፋርኛ፣ በኦሮምኛ፣ እና በሶማሊኛ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በህትመት ላይ ይገኛል ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በስፋት ከሚነገሩ እና በዩኒቨርስቲ አና በኰሌጅ ደረጃ ትምህርት በሚሰጥባቸው በሲዳምኛ፣ በሀድይኛ፣ በወላይትኛ፣ በጋሞኛ እና በከፊቾ ቋንቋዎች ትርጉሙ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በቅርብ ቀን ውስጥ ወደ ህትመት ይገባል ተብሎ የታመናል፡፡ በተጨማሪም በሐረሪ ቋንቋ ለማስተርጐም በሂደት ላይ እንገኛለን፡፡ በቀጣይም በተጨማሪ በሌሎች የሀገሪቱ ቋንቋዎች ደረጃ በደረጃ ተተርጉሞ ለመራጩ ሕዝብ የሚደርስበት ሁኔታ ይመቻቻል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ይህን ማኑዋል በመጠቀም የመራጮችና የስነዜጋ ትምህርትን ለየክልሉ ሕዝብ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ በየክልሉ የመገናኛ ብዙኃን አማካይነት በሬዲዮ በስፋት እንዲሰራጭ የአየር ሰዓት ግዢ እና የሥርጭት ውል በቦርዱ ጽ/ቤት ተፈፅሟል፡፡ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና ከፋና ብሮድካትስ ኮርፖሬት ጋር የመራጮችና የስነዜጋ ትምህርት በሬዲዮ ለአንድ ዓመት ለመስጠት የሚያስችል የውል ስምምነት ፈጽሟል፡፡

በዚህ ረገድ የትምህርቱ አሰጣጥ ዘዴ ወጥነት እንዲኖረው ከፌዴራልና ከክልል መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር የጋራ ምክክርና ውይይት ተካሂዷል፡፡ ለዚህም የሥራ ቅልጥፍና የመራጮችና የስነዜጋ ትምህርቱን ተግባራዊ ለማድረግ የቦርዱ እና የጽሕፈት ቤቱ አመራር ከሁሉም ክልል መንግሥታት ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር በመመካከር ስኬታማ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲሰጥ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡

ስለሆነም መላው የሀገራችን ህዝቦች ከጥቅምት 1 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ጀምሮ በቀጣይነት ከላይ በተጠቀሱት የክልል የመገናኛ ብዙኃን እና ሬዲዮ ጣቢያ የሚተላለፈውን የመራጮች እና የስነዜጋ ትምህርት በንቃት እንድትከታተሉት፣ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ እና ገንቢ አስተያየት እንድትሰጡበት ቦርዱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በተጨማሪም ይህንኑ ለማጠናከር በስርጭት ረገድ በስፋት ተደማጭ በሆኑት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና የሬዲዮ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት አማካይነት ትምህርቱ በሀገሪቱ ዋና ዋና ቋንቋዎች ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

መስከረም 3ዐ ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.

አዲስ አበባ፡፡

 
በ2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እና በኦሮሚያ ክልሎች የተካሄደው የማሟያ ምርጫ ውጤት ማጠቃለያ PDF Print E-mail


በ2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እና በኦሮሚያ ክልሎች የተካሄደው የማሟያ ምርጫ ውጤት ማጠቃለያ

 


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በኦሮሚያ ክልሎች የማሟያ ምርጫ እንዲካሔድላቸው በጠየቁት መሠረት፡-

1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

 • የከተማው አስተዳደር - 12
 • የክፍለ ከተማ እና - 866
 • የወረዳ ምክር ቤቶች 10,126 አባላት የማሟያ ምርጫ

2. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል

 • በሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ - 14 ቀበሌዎች

የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ ምክር ቤት አባላት ማሟያ ምርጫ

 • በቤንች ማጂ ዞን ሸኮ ወረዳ - 24 ቀበሌዎች

የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ ምክር ቤት አባላት ማሟያ ምርጫ

 • በአሌ ልዩ ወረዳ - 17 ቀበሌዎች

የወረዳ እና የቀበሌ ምክር ቤት አባላት ማሟያ ምርጫ

3. በኦሮሚያ ክልል

 • በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ - 4 ቀበሌዎች

የወረዳ እና የቀበሌ ምክር ቤት አባላት ማሟያ ምርጫ

ለማካሔድ የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሠሌዳ አውጥቶ ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት የማሟያ ምርጫው የካቲት 20 ቀን 2003 ዓ.ም. በተሳካ መልኩ ተካሂዷል፡፡

የመራጩ ሕዝብ ተሳትፎ

.

ክልል /አስተዳደር

የተመዘገበ መራጭ ሕዝብ

ድምፅ የሰጠ ሕዝብ

ድምፅ ያልሠጠ

ሴት

ወንድ

ድምር

ሴት

ወንድ

ድምር

ሴት

ወንድ

ድምር

1

አዲስ አበባ

363,104

336,879

699,983

283,756

243,453

527,209

79,348

93,426

172,774

2

ኦሮሚያ

6,021

6,994

13,015

5,937

6,851

12,788

84

143

227

3

ደቡብ ብ/ብ/ሕ

31,245

36,092

67,337

28,595

33,347

61,942

2,650

2,745

5,395

 

በጠቅላላው በአዲስ አበባ ከተማ፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እና በኦሮሚያ ክልሎች በማሟያ ምርጫ፣

የተመዘገበ መራጭ ሕዝብ

ድምፅ የሰጠ ሕዝብ

ድምፅ ያልሠጠ

ሴት

ወንድ

ድምር

ሴት

ወንድ

ድምር

ሴት

ወንድ

ድምር

400,370

379,965

780,335

318,288

283,651

601,939

82,082

96,314

178,396

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ባካሔደው 011ኛ/2003 መደበኛ ስብሰባው የካቲት 20 ቀን 2003 ዓ.ም. የተካሄደውን የማሟያ ምርጫ ውጤት መርምሮ አፅድቆታል፡፡ ውጤቱም ከዚህ እንደሚከተለው ይፋ ሆኗል፡፡

የማሟያ ምርጫው ውጤት

1. አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

 • ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለ12 የተጓደሉ መቀመጫዎች የተወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች፡-
 • ኢህአዴግ

ወንድ

9

ሴት

3

ድምር

12

 • መኢብን

ወንድ

1

ሴት

-

ድምር

1

 • ኦነአግ

ወንድ

1

ሴት

-

ድምር

1 ናቸው፡፡

 

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 12 መቀመጫዎችን ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡

 • ለክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለ866 የተጓደሉ መቀመጫዎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ወንድ 661 ሴት 205 ድምር 866 ዕጩዎች አቅርቦ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡
 • ለወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት ለ10,126 የተጓደሉ መቀመጫዎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ወንድ 6,301 ሴት 3,825 ድምር 10,126 ዕጩዎች አቅርቦ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡

2. የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል

 • ለዞን አስተዳደር ምክር ቤት ለ 10 የተጓደሉ መቀመጫዎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን - ኢህአዴግ) ወንድ 8 ሴት 2 ድምር 10 ዕጩዎች አቅርቦ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡
 • ለወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት ለ 111 የተጓደሉ መቀመጫዎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን - ኢህአዴግ) ወንድ 91 ሴት 20 ድምር 111 ዕጩዎች አቅርቦ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡
 • ለቀበሌ አስተዳደር ምክር ቤት ለ 9,030 የተጓደሉ መቀመጫዎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን - ኢህአዴግ) ወንድ 8,029 ሴት 1,001 ድምር 9,030 ዕጩዎች አቅርቦ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡

3. ኦሮሚያ ክልል

 • ለወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት ለ 12 የተጓደሉ መቀመጫዎች የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ - ኢህአዴግ) ወንድ 9 ሴት 3 ድምር 12 ዕጩዎች አቅርቦ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡
 • ለቀበሌ አስተዳደር ምክር ቤት ለ 1,200 የተጓደሉ መቀመጫዎች የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ - ኢህአዴግ) ወንድ 1,115 ሴት 85 ድምር 1,200 ዕጩዎች አቅርቦ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል፡፡

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

መጋቢት 2 ቀን 2003 ዓ.ም.

አዲስ አበባ፡፡

 

 
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ለመንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶችና ፋብሪካዎች የተላለፈ ጥሪ የካቲት 20 ቀን 2003 ዓ.ም PDF Print E-mail


ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት  ለመንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶችና ፋብሪካዎች የተላለፈ ጥሪ የካቲት 20 ቀን 2003 ዓ.ም

 


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የማሟያ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ወረዳዎች፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በወንዶ ገነት፣ በአሌ እና ሸኮ ወረዳዎች፣ በኦሮሚያ ክልል በወንዶ ወረዳ በዛሬው ዕለት የድምፅ አሠጣጡ ሂደት ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በማሟያ ምርጫው ለመሳተፍ ተመዝግበው የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ የያዙ መራጮች በዛሬው ዕለት በስራ ላይ የሚገኙ እንዳሉ ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑም በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የምትገኙ መንግሥታዊ፣ የግል ድርጅቶች እንዲሁም ፋብሪካዎች የመራጮች ምዝገባ ካርድ ይዘው የሚገኙ ሠራተኞች በምርጫ የመሳተፍ ህገ መንግሥታዊ መብታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችሉ ፈቃድ በመስጠት እንድትተባበሩ ቦርዱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፡፡

 
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማሟያ ምርጫ የድምፅ መስጫ ዕለቱን አስመልክቶ የተላለፈ ጥሪ PDF Print E-mail


ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማሟያ ምርጫ የድምፅ መስጫ ዕለቱን አስመልክቶ የተላለፈ ጥሪ

 

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 20 ቀን 2003 ዓ.ም የማሟያ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል፡፡

የማሟያ ምርጫ በሚካሄድባቸው በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ወረዳዎች፣ በኦሮሚያ ክልል በወንዶ ወረዳ፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በወንዶገነት፣ አሌና ሸኮ ወረዳዎች በነገው ዕለት መራጮች ድምጽ ይሰጣሉ፡፡

ቦርዱ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ የድምጽ መስጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶች በበቂ መጠን ተዘጋጅተው ለሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱ እንዲደርስ አድርጓል፡፡

የመራጮችና እጩዎች ምዝገባ በተሳካ ሁኔታ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናቆ መራጩ ህዝብም በአካባቢው በየደረጃው ከሚገኙ ምክርቤቶች የተጓደሉ የምክርቤት አባላትን ለማሟላት የድምጽ መስጫ ቀኑን እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ የምርጫ አስፈጻሚዎችም የህዝብ ታዛቢዎችን አሟልተው፣ የተወዳዳሪ ወኪሎችን በወቅቱ እንዲመደቡ በማድረግ እና የምርጫ ጣቢያዎችን በተገቢው ሁኔታ አደራጅተው ዕለቱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም መራጩ ህዝብ ህገ መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም በነፃነት የሚፈልገውን ተወዳዳሪ መምረጥ እንዲችልና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሁሉንም ወገኖች መልካም ትብብርና ድጋፍ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም መራጮች በነገው ዕለት ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ የምርጫ ካርዳችሁን ይዛችሁ በየተመዘገባችሁበት የምርጫ ጣቢያ በግንባር በመገኘት በነፃነት ድምፃችሁን እንድትሰጡ ቦርዱ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የካቲት 19 ቀን 2003 ..

አዲስ አበባ

 
በ2003 ዓ.ም. ለሚካሄደው ማሟያ ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ብዛት PDF Print E-mail


በ2003 ዓ.ም. ለሚካሄደው ማሟያ ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ብዛት


 

ተራ

ቁጥር

 

ክልል

የመራጭ ህዝብ ብዛት

ወንድ

ሴት

ድምር

1

አዲስ አበባ

 

331,291

360,876

692,167

2

ኦሮሚያ

 

6,941

6,044

12,985

3

ደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች

 

35,970

31,127

67,217

ጠቅላላ ድምር

 

374,832

398,047

772,369 

 
«StartPrev123NextEnd»

page 1 of 3

 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ