ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ፖለቲካ ፓርቲዎች
     
 
Banner

PDF Print E-mail

ፖለቲካ ፓርቲዎች

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ  ቁጥር 573/2000 ዓ.ም. መሠረት ተመዝግበው በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ 79 አገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዋጁ መሠረት በተናጥል፣ በግንባር፣ በቅንጅት እና በውህደት ስም ተጣምረው እንቅስቃሴያቸውን ያካሂዳሉ፡፡

 

በምዝገባ አዋጁ በግልጽ ተደንግጐ እንደሚገኘው የግንባር እና የቅንጅት አባላት የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸውን ጠብቀው ለጋራ ዓላማ  የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ውህደት የፈጸሙ ከሆነ ግን የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው በሙሉ ይቆምና በውህደቱ ስም በአንድ ፓርቲነት ይንቀሳቀሳሉ፡፡

 

በመሆኑም እነዚህ ህጋዊ እውቅና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመጪው ግንቦት ወር 2002 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ በተሰጣቸው ህገ-መንግሥታዊ መብት በመጠቀም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በዚህ መሠረት ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. ለሚካሄደው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ 49 የፖለቲካ ድርጅቶች የምርጫ ምልክቶቻቸውን በወቅቱ የመረጡ ሲሆን እነዚሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል፣ በቅንጅት እና በግንባር ስያሜ ለመወዳደር የቀረቡ ናቸው፡፡

 

 

 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ