ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ስለ ምርጫ ቦርድ አመታዊ ዕቅድ
     
 
Banner

PDF Print E-mail

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የ2002 ዓ.ም. ዕቅድ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ብሔራዊ ክልሎች የጠቅላላ፣ የአካባቢ እና የማሟያ ምርጫዎች እንዲሁም ህዝበ ውሣኔዎችን በህገ መንግሥቱና በምርጫ ህጉ መሠረት ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

በሀገሪቱ የዲሞ¡ራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁልፍና ዋነኛው ተግባር ህብረተሰቡ ነፃና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚያስተዳድረውን አካል የሚመርጥበት ሥርዓት ቀጣይነት ማረጋገጥ ነው፡፡ ቦርዱ ይህንኑ ኃላፊነቱን በብቃት መወጣት እንዲችል በተገቢው የሰው ኃይልም ሆነ በበቂ ማቴሪያል እንዲደራጅ እና እንዲጠ“ከር እየተደረገ ነው"፡ ቦርዱ በሰለጠነ የሰው ኃይል መደራጀቱ በህገ መንግሥቱና በምርጫው ህግ የተጣለበትን ኃላፊነት በተሻለ አቅም በአግባቡ በመወጣት ሀገራችን ለዲሞ¡ራሲ ሥርዓት ግንባታ ለምታደርገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ቦርዱ በመጪው 2002 ዓ.ም. ለአራተኛ ጊዜ በመላው ሀገሪቱ ለሚያካሂደው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስፈፀም የተሟላ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ በቦርዱ የተነደፉ ግቦች እና እነዚህን ግቦች የሚጠቀምባቸው የማስፈፀሚያ ስልቶች በዝርዝር ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ተግባራዊ ሆኗል::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. በአዲስ መልክ ከተቋቋመ በኋላ በ2000 ዓ.ም. የአካባቢ“ የማሟያ ምርጫን እንዲሁም በ2001 ዓ.ም. የሕዝበ ውሣኔ በማስፈፀም የተሳካ ውጤት ከማስመዝገቡም ሌላ ወደፊት ለሚያስፈፅማቸው ምርጫዎች ልምድን አጎልብቶ ለተሻለ ሥራ ከወዲሁ እንዲዘጋጅ አስችለውታል፡፡

 

I. 2001 በጀት ዓመት አፈፃፀም አጭር መግለጫ

 

-  ቦርዱ በ2001 በጀት ዓመት ለማስፈፀም በእቅድ ይዟቸው ከተከናወኑት ተግባራት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡፡

 

1. ህዝበ ውሣኔ እና ምርጫ ማስፈፀም

 

- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል እና በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች“ ሕዝቦች ክልል አዋሣኝ ቀበሌዎች ላይ ህዝበ ውሣኔ ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መልኩ ተከናውኗል፡፡ ውጤቱንም ቦርዱ አፅድቆ ለፌዴሬሽን ምክZ ቤት ቀርቦ ፀድቋል፡፡

 

- በ2ዐዐ0 ዓ.ም. በተለያየ ምክንያት ምርጫ ያልተካሔደባቸው ቀበሌዎ­ች ላይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንጌ ወረዳ 7 ቀበሌ­ዎች የአካባቢ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን በአፋር ክልል በቴሩ ወረዳ በመባይ ቀበሌ ላይ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት    ተጠናቋል፡፡

 

- በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰኔ ወር 2001 ዓ.ም. እንዲካሄድ ጥያቄ የቀረበበትን የአካባቢ“ የማሟያ ምርጫ ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችን አካሂዷል፡፡ ሆኖም ግን በክልሉ ጥያቄ መሠረት ወደ 2002 ዓ.ም.          እንዲዛወር ተደርጓል፡፡

 

2. የፖለቲካ ፓርቲዎ­ ምዝገባና ክትትል

 

- የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዲስ መልክ ለመመዝገብ ያቀረቡትን ጥያቄዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳዮችን በህጉ መሠረት መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

 

- የፖለቲካ ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ጠቃሚ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ሊያወያይ የሚያስችል መድረክ በመፍጠር ተሳታፊነታቸው እንዲረጋገጥ ተደርጓል፡፡ በዚህም ገንቢ የውይይት መድረክ ለሁሉም ተሳታፊዎች ቀደም ሲል            የነበረውን አንዳንድ አሠራር በመፈተሽና በማስተካከል የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ልምድ እንዲቀስሙ አስችሏል፡፡

 

- ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ደረጃ በደረጃ እስከ ቀበሌ ለማደራጀት ለሚደረገው ሂደት ቀደም ሲል በ2000 ዓ.ም. በቦርዱ ተዘጋጅቶ በቀረበ የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ የምክክZ መድረክ የአሠራር መመሪያ ተግባራዊ            ከመሆኑ በፊት መመሪያውን በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገምግመው የማሻሻያ ሃሣብ እንዲያቀርቡ ተደርጓል፡፡

 

3. 2ዐዐ2 .. ለሚካሔደው ጠቅላላ ምርጫ የተደረገ ዝግጅት

 

- በ2000 ዓ.ም. በተካሄደው የአካባቢ እና የማሟያ ምርጫ ላይ አገልግሎት የሰጡ እና በ2002 ዓ.ም. ለሚካሄደው አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ አገልግሎት የሚሰጡ ከፍተኛ መጠን ያላቸው የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎች፣ የምርጫ ጣቢያ        ልዩ ማህተሞች እና የማህተም መርገጫዎች ከየክልሉ እንዲሰባሰቡ እና በማዕከል እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ከፍተኛ ገንዘብ የያዘ የሂሣብ ሰነድ እንዲሰባሰብ ተደርጓል፡፡

 

- አዲስ የተጠናውን የቦርዱ ጽሕፈት ቤት ድርጅታዊ መዋቅር እና የሰው ኃይል ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ ደንብ እና መመሪያዎች እንዲሁም ቦርዱ ባወጣው የአፈፃፀም መመሪያ መሠረት ጊዜያዊ የድልድል ቡድን ተቋቁሞ የድልደላው ሥራ ተከናው“ል፡፡ በተጨማሪም በክፍት የሥራ መደቦች ማስታወቂያ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

 

- ቦርዱ የተሰጠውን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት የሚያስችለውን ክህሎት ለማዳበር በUNDP በተሸፈነ በጀት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር የአጭር ጊዜ ሥልጠና እና የልምድ ልውውጥ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

 

4. ሌሎች ተግባራት

 

- የየሩብ ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞ¡ራሲያዊ ሪፐብሊ¡ የህዝብ ተወካዮች ምክZ ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በወቅቱ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

 

- በበጀት ዓመቱ ለጽሕፈት ቤቱ ከተፈቀደው የደመወዝ እና የሥራ ማስኬጃ መደበኛ እና የህዝበ ውሣኔ ማስፈፀሚያ በጀት ተፈቅዶ ተግባር ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

 

ቦርዱ በበጀት ዓመቱ 15 መደበኛና 8 አስቸኳይ በጠቅላላው 23 ስብሰባዎችን በማካሄድ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫን ለማከናወን እና ምርጫውን በሰከነ ሁኔታ ለማካሄድ በሚያስችሉ አ­ቢይ ጉዳዮች፡-

 

-     የጽሕፈት ቤቱ ድርጅታዊ መዋቅር፣

-     የስትራቴጅክ ዕቅድ ጥናት፣

-     ሕዝበ ውሣኔ ማስፈፀም፣

-     የቦርድ አቅም ግንባታ፣

-     የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጠና እና ውይይት

 

ላይ በጥልቀት በመወያየት ውሣኔዎችን አስተላልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት በጀት አስፈቅዶ በዕቅዱ መሠረት ያከናወና¦" ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ