ራዕይ፡-
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የመምረጥና የመመረጥ መብታቸውን ነፃ፣ፍትሃዊ እና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ተግባራዊ የሚያደርጉበት ጠንካራ ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ዕውን ሆኖ ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ፡-
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህብረተሰቡን የሥነ-ዜጋ ግንዛቤ በማሳደግ ሕዝቡ የመምረጥና የመመረጥ መብቱን በአግባቡ አውቆ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቀጣይነት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማስቻል፤ በሀገሪቱ ሁሉንም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዕኩልነት ያሳተፈ ፍትሀዊ፣ ነፃና ገለልተኛ ምርጫን በህጉ መሠረት በብቃት ማስፈፀም፡፡
እሴቶች፡-
- ታማኝነት፣
- ገለልተኝነት፣
- ነጻነት እና ተጠያቂነት፣
- የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፣
- አፋጣኝ ምላሽ መስጠት፣
- በቡድን የመስራት ባህል፣
- ሀቀኝነት፣
- ተደራሽነት እና
- የሥራ ተነሳሽነት ናቸው፡፡
ዓላማዎች
የቦርዱ ጽሕፈት ቤት በቦርዱ የሚተላለፉ ውሣኔዎችን በህጉ መሠረት ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን በ2002 የበጀት ዓመት ቦርዱ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚከተሉትን ዋና ዋና ዓላማዎች ለማሳካት አቅዷል፤
- በ2002 ዓ.ም. የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በታቀደለት ጊዜ እንዲከ“ወን የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በጥራት ማከናወን፣
- ምርጫው የምርጫ ህጉን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን መሠረት አድርጎ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ማድረግ፡፡
- የፖለቲካ ፓርቲዎችን የጋራ መድረክ በማቋቋም እንቅስቃሴ እንዲጀመር“ እንዲካሄድ ማድረግ እንዲሁም አዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች በህጉ መሠረት መዝግቦ ማስተናገድ፡፡
- ለቦርዱ አባላትና ለጽሕፈት ቤቱ ኃላፊዎች እንዲሁም በየደረጃው ለሚገኙ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሙያ ክህሎት ማዳበሪያ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ የቦርዱን ጽሕፈት ቤት አቅም ማሳደግ /ማበልፀግ/፣
- የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና የማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችን በሰው ኃይል ማደራጀትና ተገቢውን ሙያዊ ስልጠና መስጠት፣
- በጽ/ቤቱ በኩል በቦርዱ የታቀዱ ተግባራትን በአግባቡ ለማስፈፀም የሚደረጉ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎችን ተግባራዊነት መከታተል፣
ከሦስተኛ ወገኖች ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ የዕለት ከዕለት ክትትል በማድረግ የሚፈለገውን ውጤት ማስገኘት፣
|