ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ መመሪያዎች
     
 
Bannerየመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2002 ዓ.ም. E-mail

ቀጣዩን ምርጫ ተቀባይነት ያለው ግልፅ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማስቻል በምርጫ ወቅት የመገናኛ ብዙኃንና ጋዜጠኞች የሚመሩበት ዝርዝር የሥነ-ምግባር ደንብ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤ የመገናኛ ብዙኃን ከምርጫ አስፈጻሚዎች የሚሰጡ ምርጫ ነክ መልዕክቶችን ሕዝቡ እንዲያውቀው በማድረግ ረገድ ያላቸውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በመረዳት፤

 

 

ወደ ኮምፒውተሩ አስቀምጥ

 

 

 


 
የመገናኛ ብዙሀን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2002 ዓ.ም E-mail

የመገናኛ ብዙሀን እና የጋዜጠኞች የምርጫ

አዘጋገብ የስነምግባር ደንብ

ቁጥር 6/2002 ዓ.ም

 

 

መገናኛ ብዙሀን በዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት ውስጥ መራጮችን በማበረታታት፣ ለመራጮች ውሳኔ የሚያግዙ የተሟሉ መረጃዎችን በማቅረብ፣ በሂደቱ ውስጥ ጉልህ ሚና መጫወት እና ከመንግስት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ ራሳቸውን ነፃና ገለልተኛ አድርገው በመንቀሳቀስ ፍትሀዊ፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ ሪፖርትና ዘገባ ማቅረብ እንዲችሉ፣

 

ወደ ኮምፒውተሩ አስቀምጥ

 

 


 
ከምርጫ ጋር ተያይዞ ለሚፈፀሙት ወንጀሎች ጋር በተያያዘ የወጣ ሕግ ከ1996 አዲሱ የወንጀል ሕግ የተወሰደ የሕግ ድንጋጌዎች የወንጀል ሕግ E-mail

ርዕስ አምስት

በሕዝባዊ ምርጫዎችና በድምፅ አሰጣጥ ላይ የሚፈፀሙ

ወንጀሎች

አንቀጽ 466 ለምርጫ የሚደረግ  ስብሰባንና  የምርጫ ሂደትን ማወክና ማሰናከል

1.  ማንም ሰው በሕግ የተፈቀደ  ከምርጫ  ጋር የተገናኘ  ሕዝባዊ   ስብሰባን ወይም

በሚመለከታቸው  ባለሥልጣኖች  ቁጥጥር በአግባቡ የሚደረግ የድምፅ  አሰጣጥን

ወይም ምርጫን  አግባብ በሌለው በማናቸውም መንገድ ያወከ፣ የከለከለ፣ ያደናቀፈ

ወይም እንዲቋረጥ ያደረገ አንደሆነ

ወደ ኮምፒውተሩ አስቀምጥ

  

 
የድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 5/2002 ዓ.ም. (የተሻሻለው) E-mail

ፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌ

 

አንቀፅ 1. አውጭው ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. አንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 19 እና አንቀፅ 110 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥ…ል፡፡

 

አንቀፅ 2. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 5/2002 ዓ.ም.” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

 

ወደ ኮምፒዩተሩ አስቀምጥ

 


 
በምርጫ ወቅት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ስለሚቋቋም የአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት እና አሠራር ደንብ ቁጥር 1/2001 ዓ.ም. (የተሻሻለው) E-mail

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የመምረጥ እና ወይም የመመረጥ መብቱን በሥራ ላይ ሲያውል በምርጫ ሂደት የሚነሱ ክርክሮችን በወቅቱ በመፍታት ሁሉም ዜጋ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በሥራ ላይ እንዲያውል ማስቻሉ ተገቢ በመሆኑ፣

 

ምርጫን ነፃና ፍትሃዊ ለማድረግ በምርጫ አፈፃፀም በየደረጃው የሚነሱ አቤቱታዎችን ተመልክቶ ወቅታዊ መፍትሄ የሚሰጥ በየደረጃው የሚቋቋመውን አካል አደረጃጀት እና አሠራር በመደንገግ በምርጫ ሂደት ለሚነሱ አቤቱታዎችና ክርክሮች አፈታት ግልፅ አሰራር ማስፈን በማስፈለጉ፣

 

ወደ ኮምፒውተሩ አስቀምጥ


Last Updated on Wednesday, 17 March 2010 18:23
 
«StartPrev123NextEnd»

 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ