|
የመራጮች ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2ዐዐ1 ዓ.ም. (የተሻሻለው) |
|
|
አንቀፅ 1. አውጪው ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡
አንቀፅ 2. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ «የመራጮች ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2ዐዐ1 ዓ.ም.» ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀፅ 3. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ@
1. «ኢ.ፌ.ዲ.ሪ» ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነው፡፡
- «ቦርድ» ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው፡፡
- «የፖለቲካ ድርጅት ወይም የፖለቲካ ፓርቲ» ማለት የፖለቲካ ፕሮግራሙን በህጋዊ መንገድ ለማራመድ በህግ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው፡፡
- «ጠቅላላ ምርጫ» ማለት አግባብ ባለው ህግ መሠረት የሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡
ወደ ኮምፒውተሩ አስቀምጥ
|