ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ምርጫ በኢትዮጵያ የመራጮች የምዝገባ ጊዜ
     
 
Banner

PDF Print E-mail

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በካሄድ ላይ ያለውን የመራጮች የምዝገባ ጊዜ መራዘም

አስመልክቶ የተሰጠ ውሳኔ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የካቲት 9 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ባካሄደው 125ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የመራጮች ምዝገባ ጊዜ እንዲራዘም ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የቀረበውን ጥያቄ እና ቦርዱ ቀደም ሲል የመራጮችን ምዝገባ በተመለከተ አቅዶት የነበረውን በጥሞና እና በጥልቀት መርምሯል፡፡

በዚህም በምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሠሌዳው መሠረት የመራጮች ምዝገባ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን በዕቅዱ መሠረት በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ የሚገኝ መሆኑን እና ይህንኑ አጠናክሮ ለተወሰኑ ቀናት ማስቀጠል የበለጠ ውጤታማ ሊሆን የሚችል መሆኑን የማረጋገጥ እና የቀረበውም የማራዘም ጥያቄ አግባብነት ያለው መሆኑን በመገንዘብ የመራጮች ምዝገባ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በዚህም የካቲት 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ይጠናቀቅ የነበረው የመራጮች ምዝገባ ጊዜ እስከ የካቲት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ድረስ የሚከናወን መሆኑን ቦርዱ ለመላው የሀገራችን ሕዝብ ያሳስባል፡፡ በመሆኑም የተራዘመውን የመራጮች ምዝገባ ጊዜ በመጠቀም እድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነው፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፣ በምርጫ ክልሉ ለ6 ወር የኖረ ሁሉ እስከ የካቲት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ድረስ በመራጭነት በመመዝገብ ካርዱን ከወዲሁ እንዲይዝ ቦርዱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ማሳሰቢያ፣

  • በየደረጃው የምትገኙ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች፣ የምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤቶችም እና የምርጫ ጣቢዎች በተራዘመው የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ሠሌዳ መራጮችን እየተቀበላችሁ በህጉ መሠረት በአግባቡ እንድትመዘግቡ ቦርድ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ፣

 

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ