ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባባር ለመገናኛ ብዘሃን ባለሙያዎች በምርጫ አዘጋገብ ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
     
 
Banner

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባባር ለመገናኛ ብዘሃን ባለሙያዎች በምርጫ አዘጋገብ ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ፡፡ PDF Print E-mail

መጋቢት 11  ቀን 2002

ቦርዱ መጪው አገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ነፃ፡ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ ብሎም በሕዝብ ዘንድ ተአማኒ ለማድረግ የማይተካ ሚና ያላቸውን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከሁሉም የአገራችን ክልሎች የተወጣጡ 12ዐ ለሚሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎች በምርጫ አዘጋገብ ዙሪያ በሁለት ዙር ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 3 እንዲሁም ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.  ከተለያዩ የሚዲያ ዘርፍ ለመጡ ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የሥልጠናው ዋና ዓላማ በአገራችን ሕዝቦች ብሎም በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በምርጫ ዙሪያ የሚወጡ ዘገባዎች የጋዜጠኝነትን ሥነ-ምግባር የጠበቁ፣ ትክክልኛ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ እንዲሆኑ የማድረግና የአገራችን መገናኛ ብዙሃን በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተገቢው መንገድ እንዲወጡ አቅም ለመፍጠረ መሆኑን ቦርዱ አስታውቆ፤  የሥልጠናው ተሳታፊዎችም በበኩላቸው  በሥልጠናው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማንሣት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የተለያዩ አገራት ተሞክሮና በምርጫ 97 የነበሩ የአወንታዊና አሉታዊ የሚዲያ ዘገባዎችን በማንሣትና ቀጣዩ የምርጫ ዘገባ ምን መምሰል እንዳለበት በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን የኢተዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ አስታወቀ፡፡

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ