ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና በድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ ላይ ስልጠና እየተካሄደ ነው።
     
 
Banner

በድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ ላይ ስልጠና እየተካሄደ ነው። PDF Print E-mail

ሚያዝያ 17 ቀን 2002

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ 2002 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ ላይ ለክልል ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊዎችና ለምርጫ ክልል ኃላፊዎች በቦርዱ የስልጠና ማእከል ዛሬ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

ስልጠናው በፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ፣ በምርጫ ታዛቢዎችና የፓርቲ ወኪሎች ሚና፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ የፖሊስና የምርጫ ስነስርዓት አስከባሪዎች ሚና፣ በድምፅ አሰጣጥ ዝግጅት እና የድምፅ መስጫው ዕለት የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እንዲሁም የድምፅ ቆጠራ ዝግጅት፣ የቆጠራ ሂደት፣ የቆጠራ ውጤት አሞላልና አገላለፅ ሂደት እና የመሳለሰሉት ትኩረት አድርጎ እንደሚሰጥ የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር መርጋ እንደተናገሩት በመላ ሃገሪቱ ከ31 ነጥብ 9 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በመራጭነት ተመዝግቦ ድምጹን ለመስጠት የምርጫ ካርዱን በእጁ በማስገባት የምርጫውን ቀን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም  63 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘንድሮ ምርጫ ለመወዳደር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ሺ 178፣ ለክልል ምክር ቤት 4ሺ 730 ዕጩዎችን ማስመዝገባቸው፣ በግል ደግሞ 31 ዕጩዎች እንደተመዘገቡ ጠቅሰው በመላ ሃገሪቱ በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር 6ሺ 939 ዕጩዎች ተመዝግበው የምርጫ ዘመቻቸውን በሕጉ መሰረት በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ሰልጣኞቹ በፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ላይ ባደረጉት ውይይት እንደገለፁት አዋጁ ተግባራዊ በመደረጉ በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ መቋቋማቸው የቅሬታ አፈታት ሂደቱን እንዳቃለለውና ለምርጫ አስፈፃሚዎችም የስራ ጫና እንደቀነሰላቸው አብራርተዋል።

ይህ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ስልጠና ከ 300 በላይ ሰልጣኞች እየተካፈሉ ሲሆን ሰልጣኞቹ ከትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ጋምቤላ፣ እና ሃረሪ ክልሎች እንዲሁም ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተገኝተዋል። ከዚህ ስልጠና ማጠናቀቂያ በኋላ ለሌሎች ክልሎችም ስልጠናው እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ