ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና በድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ ላይ ሲካሄድ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ
     
 
Banner

በድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ ላይ ሲካሄድ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ PDF Print E-mail

ሚያዝያ 18ቀን 2002 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ2ዐዐ2 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ ሊያካሄድ የቀደውን አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ፣  አቆጣጠር እና የውጤት አገላለፅ አፈፃፀም ሂደት ላይ ለክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እና የምርጫ ክልል ምርጫ ጽሕፈት  ቤት ኃላፊዎች  በማዕከል ሲሰጥ የቆየው የመጀመራያው ዙር ሥልጣና ዛሬ በተሳካ መልኩ ተጠናቀቀ፡፡.

የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ከ300 በላይ ለሚሆኑ  የሥልጣናው ተሳታፊዎች  እንደገለጹት መጪውን ምርጫ ነፃ፡፡.ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በመላው ሀገራችን ሕዝቦች አመኔታ ባተረፈ መልኩ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ በቦርዱ የተጣለባችሁ ኃላፊነትና በመላው የሀገራችን ሕዝቦች፣ በተወዳዳሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠበቅባችሁ የአፈፃፀም ብቃትና ገለልተኝነት ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣

እስካሁን በሥልጠና ቆይታችሁ በምርጫ ክልላችሁ ሥር በሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች ብዛት እና ዝርዝር መሠረት ሰናድና ቁሳቁስ መታሸጋቸውን፣የታሸገው የድምፅ መስጫ ወርቀት ላይ የታተመው የዕጪዎች ስም እና ምልክት ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምከር ቤቶች በምርጫ ክልላችሁ ቀደም ሲል በካሄዳችሁት ምዝገባ መሠረት መሆኑን ከጽሕፈት ቤቱ የሎጅስቲክስ ዋና ክፍል ባለሙያዎች ጋር እንደተናበባችሁና ትክክለኛነቱን በፈርማችሁ እንዳረጋገጣችሁ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል ፡፡

በመጨረሻም ወደ የምርጫ ክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ የምርጫ አሰፈፃሚዎችን፣ የሕዝብ ታዛቢዎችን፣ የዕጩ ወኪሎችንና በተለይም ደግሞ መላውን መራጭ ሕዝብ ተገቢውን ሥልጠና እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በመስጠትና የምርጫ ጣቢያዎች፣የምርጫ አስፈፃሚዎች በወቅቱ ተደራጅተውና የዕጩ ወኪሎች በህጉ መሠረት ከወዲሁ ተሟልተው እንዲገኙ ጥሪ በማድረግና የዝግጅት ሥራዎችን እንዲያካናውኑ አስፈላጊውን ሁሉ ማደረግ ይኖርባችዋል ሲሉ የምርጫ ቦርደ ሰብሳቢ ክበር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ተናግራዋል ፡፡

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ