ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና ለክልል ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊዎች እና ለምርጫ ክልል ኃላፊዎች ሁለተኛ ዙር ስልጠና ተጀመረ።
     
 
Banner

ለክልል ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊዎች እና ለምርጫ ክልል ኃላፊዎች ሁለተኛ ዙር ስልጠና ተጀመረ። PDF Print E-mail

ሚያዝያ 22ቀን 2002ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ ላይ ለክልል ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊዎችና ለምርጫ ክልል ኃላፊዎች በቦርዱ የስልጠና ማእከል ዛሬ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ስልጠናውን በንግግር የከፋቱት የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ሲሆኑ በንገግራቸውም ሥልጠናው የሚያትኩርባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች በመዳሰስ በፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ፣ በምርጫ ታዛቢዎችና የፓርቲ ወኪሎች ሚና፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ የፖሊስና የምርጫ ስነስርዓት አስከባሪዎች ሚና፣ በድምፅ አሰጣጥ ዝግጅት ፣ የድምፅ መስጫው ዕለት የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እንዲሁም የድምፅ ቆጠራ ዝግጅት፣ የቆጠራ ሂደት፣ የቆጠራ ውጤት አሞላልና አገላለፅ ሂደት እና የመሳሰሉት ትኩረት አድርጎ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

 

 

በድምፅ መስጫው ዕለት ስለሚከናወኑ ተግባራት፣ ስለሰነድና ቁሳቁስ አጠቃቀም፣ ስለድምፅ ቆጠራው እና ማዳመሩ፣ እንዲሁም የውጤት አሞለል እና አገላላጽ ስልጠና ባስራጨናቸው ልዩ የምርጫ አፈፃፀም ደንብና መመራያዎች፣ ከማዕካል ለየምርጫ ጣቢያው የተለኩትን ሰነድና ቁሳቁሶች በአግባቡ ለየምርጫ ጣቢያው እንድታሰራጩ ፣ ከድምፅ አስጠጡ ሂዳት በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ በአግባቡ ወደ ማዕከል መመለስ፣ የምርጫ ጣቢያ ልዩ ማህተም፣ የማህተም መርገጫ የድምፅ መሰጫ ኮሮጆ፣ ፒንሳዎች እና ሌሎች ትራፊ ቀለሞችን በጥንቃቄ ወደ ማዕከል መመለስ እንዲሁም የጠቅላላ ምርጫ የድምፅ ቆጠራ ውጤት ከየምርጫ ጣቢያው በሕዝብ ተወካዩችና በክልል ምክር ቤት አንፃር በአግባቡ አጠናክረው ለቦርድ በወቅቱ መላክ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

 

በመጨረሻ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ስልጠና ከ 300 በላይ ሰልጣኞች እየተካፈሉ ሲሆን ሰልጣኞቹ ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  ክልል  ተገኝተዋል። ከዚህ ስልጠና ማጠናቀቂያ በኋላ  ተመሳሳይ ስልጠናዎች ለተቀሩት የሶማሌ ክልል ፣ለከፍተኛ ትምሀርት ተቌማት፣ ለዩኒቨርስቲ ተማረዎች፣ ለኮሌጆች አና ለመከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሚሰጥ ተውቌል።
 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ