ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና ለመከላከያ ሠራዊት እና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርጫ አስተባባሪዎች ሥልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
     
 
Banner

ለመከላከያ ሠራዊት እና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርጫ አስተባባሪዎች ሥልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡ PDF Print E-mail

ሚያዚያ 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. አገራችን በለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ምርጫ አፈፃፀም በተመለከተ ለመከላከያ ሠራዊት እና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርጫ አስተባባሪዎች ሥልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡

የቦርዱ ሰብሰቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና 140 ለሚሆኑ የሥልጠናው ተሳታፊዎች እንደገለፁት በዛሬ እለት የሚጀምረውና በተከታታይ ለሦስት ቀናት በሚሰጠው ሥልጠና ላይ በዋነኛነት በድምፅ አሰጣጥ፣ ዝግጅት እና በድምፅ መስጫው ዕለት የድምፅ አሰጣጥ ሂደት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በተመለከተ በምርጫ ጣቢያ እና በምርጫ ክልል ደረጃ በማሳያ የተደገፈ፣ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው አሠራርን ከሀገራችን የምርጫ አሠራር ጋር በማነፃፀር በምርጫ አፈፃፀምና በውጤት አገላለፅ፣የሰነድና ቁሣቁስ  አጠቃቀምን፣ የተመደበ በጀት ዝርዝር ና አጠቃቀም እንዲሁም የሂሳብ አያያዝና ሂሳብ ማወራረድ በተመለከተ መነሻ ሐሳቦችን ያከተተ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመጨረሻም ምርጫውን ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በሕዝብ  ዘንድ አመኔታ ያተረፈ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በምርጫ ሕጉ፣ ደንብና መመሪያዎቹ መሠረት ብቻ መሥራት እንዳለባቸው አሳስበው፣ ወደየተቋማችሁ በምትመለሱበት ጊዜ የየምርጫ ጣቢያው የምርጫ አስፈፃሚዎችን በተለይም መራጩን ሕዝብ፣ የእጩ ተወዳዳሪ ወኪሎችን፣ የምርጫ ጣቢያ የሕዝብ ታዛቢዎችን፣ የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎችን በተገቢው አክብሮትና  በተለመደው ጨዋነት የተሞለበት ኢትዮጵያዊነት ባሕላችን መሠረት ማስተናገድ ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ