|
የናይጀሪያ ልዑካን ከምርጫ ቦርድ ጋር ተወያዩ። |
|
|
|
|
ነሐሴ 10 ቀን 2002 ዓ.ም.
የ2002 ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ በሆነ መንገድ መካሄዱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ ሰብሳቢ ገለፁ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንደተናገሩት ለ 2002 ምርጫ መሳካት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ ተወዳዳሪዎችና የግል ዕጩዎች እኩልና የተስተካከለ የውድድር ሜዳ ተዘጋጅቶ 63 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፋቸውን ገልፀዋል።
ምርጫ ጣቢያዎች በተሻሻለው የምርጫ ሕግ መሰረት ከ አንድ ሺ በላይ ህዝብ ባለማስተናገዳቸውና ረጅም ሰልፍ ባለመኖሩ ህዝቡ ብዙ ጊዜ ሳይፈጅ እንደመረጠና ከተመዘገበው 31 ነጥብ 9 ሚልዮን በላይ ህዝብ 29 ሚልዮን 832 ሺ 91 ህዝብ ድምፅ ሰጥቷል። ከዚህ በተያያዘም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነምግባር ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 662/2002 ዓ.ም የምርጫ ስነምግባር ደንብ በምርጫው ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ቅሬታዎች ፓርቲዎች ራሳቸው በራሳቸው ተመካክረው እንዲፈቱ ያደረገ አዋጅ በመሆኑ የቅሬታ ሂደቱ ቀላል እንዳደረገው ፕሮፌሰሩ አክለው ገልፀዋል።
የናይጀሪያ ልዑካኑ ከተለያዩ የመንግስት መስሪያቤት የተውጣጡ ናቸው። በምርጫው ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው በቦርዱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢና የፅሕፈት ቤቱ ዋና ሃላፊ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። |