ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍ አደርገ
     
 
Banner

ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍ አደርገ PDF Print E-mail


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2ዐዐ3 በጀት ዓመት አስመልክቶ በሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች መቀመጫ ላላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች የዕለት ከዕለት የፋይናንስ ድጋፍ ክፍፍል አደርገ፡፡

ቦርዱ የተሻሻለውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2ዐዐዐ ዓ.ም አንቀፅ 42 ንዑስ አንቀፅ 1 እና አንቀፅ 45 ንዑስ አንቀፅ 1 መሠረት በማድረግ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠው ድጋፍ በፌዴራል ወይም በክልል ምክር ቤት ባላቸው መቀመጫ ብዛት መሠረት እንደሆ ይደነግጋል፡፡ በዚህ መሠረት በበጀት ዓመቱ ከመንግሥት አሥር ሚሊዮን (1ዐ,ዐዐዐ.ዐዐዐ) ብር አስፈቅዶ በህጉ መሠረት በሕዝብ ተካዮች ምክር ቤት የሕዝብ ውክልና ላቸው አሥር የፖለቲካ ድርጅቶች ተከፍሏቸዋል፡፡በሁለቱም ምክር ቤቶች የተያዘ መቀመጫ ብዛት 2,779 መቀመጫ ሲሆን ለእያንዳንዱ መቀመጫ የሚደርሰው ብር ሦሰት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ስምንት ከአረባ አንድ (3,598.41) ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡

የሕዝብ ውክልና ያላቸው እና የዕለት ከዕለት የፋይናንስ ድጋፍ ከመንግሥት የተደረገላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ገንዘቡን በወጪ አርዕስት በመዘርዘር በሕጉ መሠረት ለታቀደለት ዓላማ ለማዋል ለኦዲተር የተረጋገጠ ወቅታዊ ሪፖርት ለቦርዱ ማቅረብ አለባቸው ከተሰጣቸው ገንዘብ ያልተጠቀሙበትን በወቀቱ የመመልስ ግዴታ ያለባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ቦርዱ በ2ዐዐ2 ዓ.ም ለተደረገው ጠቅላላ ምርጫ እንቅስቃሴ የሚሆን በምርጫ ለተሳተፏ የፖለቲካ ድርጅቶች በህጉ መሠረት የበጀት ድጎማ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ