ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና በድህረ ምርጫ ዳሰሳ ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ
     
 
Banner

በድህረ ምርጫ ዳሰሳ ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ PDF Print E-mail

መጋቢት 22 ቀን 2003ዓ.ም.

በኢትዮጵያ የተካሄደው የ2002 ዓ/ም 4ኛው ዙር ድህረ ምርጫ አፈፃጸም ዳሰሰ ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ላይ ወርክሾፕ እያካሄደ መሆኑን  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና  የድህረ ምርጫ ግምገማ ረቂቅ ሪፖርቱን ለማዳበር ለባለድርሻ አካላት  በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ እንደገለጹት  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦና ተመካክሮ በመስራቱ በ2002 ዓ/ም የተካሄደው 4ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ከምንጊዜውም በላቀ መልኩ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ  በሆነ መንገድ ሊጠናቀቅ ችሏል።

እንደ ፕሮፌሰር መርጋ ገለፃ ወደፊት በአገራችን የሚካሄዱ ምርጫዎችም በየትኛውም መለኪያ አለም አቀፍ ደረጃቸው የበለጠ ከፍ እያለ እንዲሄድ ለማድረግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ መሰረት ቦርዱ በየጊዜው የሚደረጉ ምርጫዎች አፈፃፀምና የምርጫ ህጎችን የመገምገም፣ ጥናት ማካሄድ እና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን  ጉዳዮች ለይቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የማቅረብ ተግባርና ሃላፊነቱን ለመወጣት ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። በምርጫው አፈፃፀም ላይ የታዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ለመለየት ባለድርሻ አካላትን በግንባር ቀደምትነት ባሳተፈ መልኩ እየተካሄደ የሚገኘው የ2002 ድህረ ምርጫ ግምገማ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ነው የቦርድ ሰብሳቢው ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ያስረዱት።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር በበኩላቸው  የ2002 ድህረ ምርጫ ግምገማ  በምርጫው ወቅት የተከሰቱ እና የታዩ ጉድለቶችን በዝርዝር በመለየት የተገኙ በጎ ልምዶችን እና ተሞክሮዎችን በማጠናከር በቀጣዮቹ የምርጫ ሂደቶች የተሻለ የአሰራር ስልት በመንደፍ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ነው ብለዋል።

በወይይቱ የተሳተፉት ባላድርሻ አካላትም በዳሰሰ ጥናቱ ረቂቅ ሪፖርት ላይ በጥልቀት በመወያየት ገንቢ የሆኑ አስተያየቶችን በመስጠት ሰነዱን አዳብረውታል። ከበላድርሻ አካላት የተሰጡትን  ገንቢ አስተያየቶች ተካቶ በቦርዱ ከፀደቀ ቦኃላ የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት ለተዎካዮች ም/ቤት የሚቀርብ መሆኑ ታውቋል።

በግዮን ሆቴል በተካሄደው ውይይት 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና  ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ  ]lr ባለድርሻ አካላት  ከ90 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ለሶስት ተካታተ¨ d~r l’YŒcፑ Fይ ተገኝቷል።

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ