ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/ ሥልጠና ተሠጠ::
     
 
Banner

የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/ ሥልጠና ተሠጠ:: PDF Print E-mail

ግንቦት 9 ቀን 2003 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትና በየደረጃው የሚገኙ የጽ/ቤቱ ኃላፊዎች መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ለማካሄድ የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ደብረዘይት ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ማሠልጠኛ ተቋም ተሰጠ፡፡

የሥልጠናው ዋና ዓላማ ቦርዱ በ2ዐዐ3 ዓ.ም በያዘው ዕቅድ መሠረት የመሠረታዊ ሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/ ለማካሄድ የሚያስችል የ BPR ሥልጠና በመውሰድ መሠረታዊ እውቀት ለመጨበጥ ያለመ ነው፡፡

ሥልጠናው በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/ መሠረታዊ ፅንሠ ሃሳብ በማተኮር፣ በአገራችን BPR ካካሄዱ መ/ቤቶች የተገኙ ተሞክሮዎችን፣ በተግባር የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዲሁም እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል በምሳሌ በማስደገፍ ሠልጣኞች በቀላሉ እንዲረዱትና ለተግባራዊነቱ እንዲዘጋጁ በሚያስችል አቀራርብ መሠጠቱን ሠልጣኞች ተናግረዋል፡፡

በሥልጠናው ላይ ሠልጣኞቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሣት ሥጋታቸውንና የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች፣ የኮሜቴዎችን አወቃቀር፣ የበላይ ኃላፊዎችን ሚናና የሥራ ሂደቶችን እንዴት መለየት እንደሚቻል እና ለመ/ቤቱ ሠራተኞች በየጊዜው መረጃ መስጠት ስለሚቻልበት ሁኔታ በማንሳት ንቁ ተሣትፎ የታየበትና በቂ እውቀት የጨበጡበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሥልጠናው ከግንቦት 1 እስከ 5/2ዐዐ3 ዓ.ም ድረስ የተሰጠ ሲሆን በሥልጠናው ላይ የቦርዱ አባላት፣ የጽ/ቤቱ ኃላፊዎች፣ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የጽ/ቤቱ መምሪያ ኃላፊዎች በጠቅላላ 26 ሠልጣኞች  መሳተፋቸውን ከሥልጠና ማዕከሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህ ሥልጠና በየደረጃው የሚገኙ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በቀጣይ የሚያገኙት መሆኑን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ