|
ቦርዱ ለምርጫ አስፈፃሚዎች የምስክር ወርቀት መስጠት ጀመረ |
|
|
|
|
ግንቦት 7 ቀን 2003 ዓ∙ም (አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ2002 ዓ∙ም ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማስፈፀም በምርጫ ስራ ላይ ለተሰማሩ የምርጫ አስፈፀሚዎች የማበረታቻ የምስክር ወረቀት መስጠት መጀመሩን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መንገሻ አስታወቁ።
ኃላፊው እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2002 ዓ∙ም የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ሰላማዊ፣ዴሞክራሲዊ እና በህዝብ ዘንድ አመኔታን ባተረፈ መልኩ መጠናቀቁን አስታውሰው፤ የምርጫ አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና የምርጫ
አስፈጸሚዎችም የማስፈጸም ብቃት እየጨመረ መሆኑን በመግልፅ፤ ለዚሁ አስተዋፅኦ ቦርዱ በየደረጃው ለሚገኙት የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለመከላከያ ሠራዊት ምርጫ አስፈጻሚዎች ደረጃውን የጠበቀ የምስጋና ምስክር ወረቀት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድርጉን ገልፀዋል።
ስለሆነም አራተኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ ካስፈጸሙት ምርጫ አስፈፃሚዎች መካከል እስካሁን ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና አንድ (206391) ለሚሆኑ ምርጫ አስፈፀሚዎች ከግንቦት 6 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የምስክር ወርቀት በሁሉም የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በኩል እንዲደርሳቸው መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። |