ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና ቦርዱ የመራጮችና ስነ-ዜጋ ትምህርት በዘላቂነት ለመስጠት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ስምምነት አደረገ
     
 
Banner

ቦርዱ የመራጮችና ስነ-ዜጋ ትምህርት በዘላቂነት ለመስጠት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ስምምነት አደረገ PDF Print E-mail

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮችና ስነ-ዜጋ ትምህርት ለማሳደግ የሚያስችል  ከሁሉም ክልል የመገናኛ ብዙሃን  ጋር  ለአንድ ዓመት የሚቆይ  የውል ስምምነት አደረገ።

የቦርዱ ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ረዳት ኃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ እንደገለጹት ለቦርዱ ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባር አንዱ ምርጫን አስመልክቶ ለህዝቡ የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት በስፋት የመስጠት እና ትምህርቱን ለሚሰጡ አካላት ደግሞ ፈቃድ የመስጠት፣የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ገልፀዋል ። ቦርዱ በተለያዩ ጊዜያት ባለድርሻዎችን በመጋበዝ  በሥነ-ዜጋና በመራጮች ትምህርት ላይ ሙያዊ አስተያየቶቻቸውን እንዲሰጡ

ተደርጎ በማኑዋሉ እንዲካተቱ ተደርገዋል ብለዋል።

ስለሆነም በሁሉም የክልል  መገናኛ ብዙሃን   በሬድዮ ስርጭት በሳምንት ሁለት ጊዜ ለአንድ ሰዓት በየክልሉ የሥራ ቋንቋዎች እንደሚተላለፍና ተከታታይነት ያለው መሆኑን ረዳት ኃላፊው አክለው ገልፀዋል።

ይህ የመራጮችና ስነ-ዜጋ ትምህርት ለተለያዩ ተቋማት ለትምህርታዊ ድጋፍ ሰጪነት እና ለጥናታዊ ፁሑፎች ለመረጃነት እንደሚያገለግል ለማወቅ ተችሏል።

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ