ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሁለንተናዊ ለውጥ አመራር ላይ ሁለተኛ ዙር ሥልጠና ሰጠ
     
 
Banner

ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሁለንተናዊ ለውጥ አመራር ላይ ሁለተኛ ዙር ሥልጠና ሰጠ PDF Print E-mail

ሰኔ 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሁለንተናዊ ለውጥ አመራር ላይ የሁለተኛውን ዙር ሥልጠና በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ማሰልጠኛ ማዕከል በቢሸፍቱ ከተማ መስጠት ጀመረ፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና የሥልጠናውን ዓላማ ሲገልፁ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቅም ለመገንባት በሀገራችን የተጀመረውን የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት በይበልጥ በማጠናከርና ወደተሻለ ደረጃ ከማድረሱም በተጨማሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያካበቱትን የተለያየ ልምድና ሃሳብ የሚለዋወጡበት ሆኖ እንደሚያገለግል እምነታችውን ገልፀዋል፡፡

ቦርዱ ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት በአበይት ወቅታዊ ጉዳዩች ማለትም በግጭት አፈታት፣ በሰላማዊ የምርጫ ውድድርና መሰል ሁኔታዎች፣ በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ፣ በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ህግ እና እነዚህን ህጐች መሠረት በማድረግ በወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ለፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ሰብሳቢው አሰታውሰው ለወደፊቱም በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ሥልጠናው ለ5 ተከታታዩ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በሥልጠና ቆይታቸው ሁለተናዊ ለውጥ አመራር ሚና ምን መሆን እንዳለበት ከተለያዩ ሀገሮችና ከአገራችን ልምድ ጋር የተገናዘበ እውቀት ያገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሥልጠናው ላይ ከ37 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

40 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በሁለንተናዊ ለውጥ አመራር ላይ በአንደኛው ዙር ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 1ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም መሰልጠናቸው ይታወቃል፡፡

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ