|
በ2004 ዓ.ም በጀት እቅድ ላይ ወይይት ተካሄደ |
|
|
|
|
ሰኔ 28 ቀን 2003 ዓ∙ም
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አደራሽ የ2004 ዓ.ም በጀት ረቂቅ እቅድ ላይ ከአጠቃላይ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መንገሻ የውይይቱን አላማ ሲገልጹ እንደተናገሩት የ2004ዓ.ም በጀት የቦርዱን የሥራ እቅድ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች፣መምሪያዎች እና ዋና ክፍሎች በኩል የታቀዱትን አመታዊ ረቂቅ እቅድ ላይ ያልተካተቱ ካሉ ለመጨመር የሚቀነሱም ካሉም ለመቀናስና ሰራተኛው የባለቤትናት ስሜት ኖረት እንዲሳተፉ ለማደርግ መሆኑን ገልፀዋል። የእቅዱ መነሻም የቦርዱ የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ በዋነኛነት የተወሰደ ሲሆን በዘርፎቹ ሥር የሚገኙ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚዳስሱም ጠቁመዋል።
በዚሁ መሠረት በጽ/ቤቱ ሥር የሚገኙ የአገልግሎቶች እና ግንኙነት ዘርፍ እና የድርጅታዊ ድጋፍ ዘርፍ እያንዳንዳቸው የ2004ቱን በጀት አመት በቁልፍ ተግባር እና በዝርዝር ተግባር አቅርበዋል። በአገለግሎቶች እና ግንኙነት ዘርፍ ከቀረቡት ዋና ዋናዎቹ ውስጥ የውጤት ተኮር አፈፃፀም፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባን መርምሮ መወሰን፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተቀለጠፈ እና ምቹ የመረጃ አገለግሎት እንዲኖር ማድረግ፣ በሕዝብ ግንኙነት ሥራ ስለ ቦርዱ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ሰፊና የማያቋርጥ መረጃ ለህብረተሰቡ በማቅረብ የማሳወቅ፣የማስተማር እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መስራት፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በመሆን የምርጫ ክልል በአዲስ መልክ ማካለል እና ለ2005 ማሟያ ምርጫ ቅደመ ዝግጅቶችን ማከናወን የሚሉ ተጠቅሰዋል። በሌላ በኩል በድርጅታዊ ድጋፍ ዘርፍ ከቀረቡት ዋና ዋና ተግባራቶች ውስጥ የቦርዱን የፋይናንስ ንብረት አያያዝ እና አጠባበቅ እንዲሁም ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ የሰው ኃይል፣ ሥልጠና እና አቅም ግንባታ መለየት፣የግዥ እቅዶችን በተገቢው ሁኔታ ማቀድና የመንግስት የአሠራር ስርዓትን በጠበቀ ዲሲፕሊን መከተል የሚሉት ይገኙበታል። በአጠቃላይ ከውውይቱ ተሳታፊዎች የተነሱት አስተያየቶች በተመለከተ እቅዶቹ በየሥራ ዘርፎቹ መታቀደቸው የሚበረታታ እና አሁንም ጽ/ቤቱ ዘመናዊ የአሠራር ሥልቶችን ሊከተል እንደሚገባ፣ ለሠራተኛው ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር እና ጥቅም ማስከበር የሚሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በኃላፊዎች ማብራሪያ ተሠጥቶባቸዋል። ረቂቁ እቅድ ለቦርዱ ቀርቦ ከፀደቀ በኃላ ሥራ ላይ እንደሚውል ታውቋል። |