|
ቦርዱ በውጭ ሀገር የልምድ ልውውጥ አደረገ |
|
|
|
|
ሰኔ 29 ቀን 2003 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፍተኛ አመራሮች በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና ሜክሲኮ ሀገሮች ለሁለት ሳምንት የቆየ የልምድ ልውውጥ አጠናቀው መመለሳቸውን ጽ/ቤቱ አስታወቀ።
የቦርዱ ኃላፊዎች በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት በሜክሲኮ አለም አቀፍ አውደ ጥናት ላይ የተሳተፉ ሲሆን የሀገራችንን የምርጫ ተሞክሮ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል። ከቀርቡት የአገራችን የምርጫ ተሞክሮዎች ውስጥ በቅሬታ አፈታት፣ በሥነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት አሰጣጥ፣ የቦርዱ አሠራር እና ተግባር ምን እንደሚመስል፣ በምርጫ ቁሳቁስ (Logistics) አዘገጃጀትና ስርጭት በአውደጥናቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።
ከሜክሲኮ የምርጫ አሠራር የተገኙ ተሞክሮዎች በተመለከተ የምርጫ ኮሚሽኑ አወቃቀር እና አደረጃጀት፣ የቅሬታ አፈታትና አወሳሰን፣ የመራጮች የምዝገባ ስርዓት፣ የመራጩን ሥነ ዜጋዊ እውቀት ለማሳደግ እና ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ሥልጠና የሚሰጥበት ሁኔታ እና በምርጫ ወቅት ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በኩል ያሉ ተሞክሮዎችን በማየት በቂ ግንዛቤ ተገኝቷል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በዋሽንግተን ዲሲ IFES (International Foundation for Electoral System) የተባለ ድርጅት በምርጫ አሰራርና አስተዳደር (Election Management & Administration) ላይ ያላቸውን ልምድ በስፋት ያካፈሉ ሲሆን ድጋፋቸውን አጠናክሮ ለመቀጠል አፍሪካ ህብረት ዋና ፅ/ቤት በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ቋሚ ጽ/ቤት እንደገና ለመክፍት በዝግጅት ላይ መሆኑን ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል።
ቦርዱ የተገኙ ተሞክሮዎችን ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የህግ ማዕቀፍና የኢኮኖሚ አቅም ጋር እየታየ ተሞክሮውን ወደ ሃገራችን ለማምጣት ወደፊት አስፈላጊው ጥረት እንደሚያደርግ ጽ/ቤቱ አስታውቌል፡፡ |