|
ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የጋር ምክክር አደረገ |
|
|
|
|
ህዳር 21 ቀን 2004 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖሊቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ.ም የጋር ምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ አካሄደ። የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በምክክር መድረኩ ላይ አንደገለፁት ቦርዱ ባለፉት ሁለት አሥርት አመታት የጠቅላላ ፣ የአካባቢ፣ የማሟያ ፣ የድጋሚ ምርጫ እና የህዝብ ውሳኔዎችን ነፃ፣ ፍትሃዊና በገለልተኝነት በማስፈጸም የተጣለበትን ህዝባዊና አገራዊ አደራ በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን እና ቦርዱ በህገመንግሥታችን፣ በምርጫ ህግ እና በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ህግ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እየመዘገበ ፣በህጉ መሠረት እየተከታተለና እያስተናገደ ይገኛል ብለዋል፡፡
ፓርቲዎች የሕግን የበላይነት የመጠበቅና የማስጠበቅ፣ለሕዝቡም የማስረዳት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ህግ በ2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሻሽሎ ከመውጣቱ ጋር ተያይዞ እና አብዛኞቹ ፓርቲዎች የተደራጁት ይህ አዋጅ ከመሻሻሉ በፊት በመሆኑ በአዋጁ የተደነገጉ መሠረታዊ ጉዳዮችን ሙሉ በሙሉ ሲተገብሯቸው አይስተዋሉም በማለት የቦርዱ ሰብሳቢ ጨምረው ገልጿል፡፡ ይህም የአዋጁን ድንጋጌዎች ጠንቅቆ ካለመገንዘብ ሊመነጭ እንደሚችል ገልፀው ቦርዱ በህጉ መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብና የመከታተል ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሻሻለው የምርጫ ህግ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን በሙሉ ጠንቅቀው በመረዳት አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ሀገራችን ፍትሐዊ፣ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ሥርዓት ለማስፈን የወጡትን የሕግ ማዕቀፎች በአንድ ላይ ጠቅለለል አድርገን በማዘጋጀት በቀላሉ እንድታገኙዋቸውና እንድትጠቀሙባቸው በማድረግ የነበሩ ችግሮች ይቀረፋሉ ተብሎ ይጋመታል ብለን እናምናለን ብሎዋልፕሮፌሰር መርጋ የቦርዱ ሰብሳቢ፡፡
የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ኃላፊ የአገልግሎቶችና ግንኙነት ዘርፍ አቶ ኤርምያስ አሰፋ በበኩላቸው ለተሳታፊዎች የመወያያ ፁሑፍቸውን በማቅርብ በተለይም በተሻሻለው የፓሊቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ 573/2000 ዓ.ም በሚደነግገው መሠረት ፖለቲካ ፓርቲዎች በአጠቃላይ ሰለ ወቅታዊ የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎቻቸውን የሚያስገመግም መጠይቆች ለያንደንዱ ፓርቲዎች በማቅረብ ከቀረቡት መጠይቆች በኦዲተር የተረጋገጠና በፓርቲ መሪ የተፈረመ ሃብትና እዳ ሰነድ ማቅረብ ፤ፓርቲው ያሉትን ጽ/ቤቶች አድራሻ እና ኃላፊዎች ማሳወቅ፤ በፖሊቲካ ፓርቲው የተመረጠ አዲስ የአመራር አባለት ዝርዝር ማሳወቅ በተለያዩ ምክንያት የፓርቲው አመራር አባላት የተጓደሉ ከሆኑ እና ቁጥሩ ከ50%+1 በታች ከሆነ በ30 ቀናት ውስጥ መሟላት፤ በሕጋዊ አካል የተረጋገጠ የሞያ ብቃት ያለው የተሾመ የውጭ ኦዲተርና ሹመቱን መቀበሉን በፊርማው ያረገገጠበት ሰነድ ለቦርዱ ሪፖርት ማድረግ ፤ለ2002 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የተሰጠውን ድጋፍ በኦዲት የተረጋገጠ ሪፖርት ማድረግ እና ከ2002 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ራሱን ያገለለ በመሆኑ የተሰጠውን ድጋፍ በአግባቡ ሪፓርት ያለደረገ የሚሉ መጣይቆች ነበሩ፡፡ በዚሁ መሠረት እያንዳንዱ የፓሊቲካ ፓርቲ ምላሹን በመጠይቆቹ መሰረት ለቦርዱ ያቀረቡ ሲሆን ከ76ቱ የፓለቲካ ፓርቲዎች በትክክል ለቦርዱ ሪፖርት የደረጉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢሕአዲግ/ እና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ /ኢራፓ/ መሆናቸውን ተገልጿል፡፡
በመጫረሻም አብዛኛው ፓርቲዎች ያላቸውን ክፍተት ለመሙላት ጥረት እንደሚያደርጉ እና ቦርዱ የጀመረውን ክትትል እና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል በመስማማት የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡ የምርጫ አፈፃፀሞች ሕግን መሠረት በማድረግ ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በተለይም በአዋጆች፣ በደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ቦርዱ አዘጋጀቶ ሲሰጥ ቆይቷዋል፡፡ |