ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና ማህበራት በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና በአገራዊ አመለካከት ላይ ግንዛቤመፍጠር እንዳለባቸዉ ተገለጸ
     
 
Banner

ማህበራት በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና በአገራዊ አመለካከት ላይ ግንዛቤመፍጠር እንዳለባቸዉ ተገለጸ PDF Print E-mail

ማህበራት በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና በአገራዊ አመለካከት ላይ ግንዛቤመፍጠር እንዳለባቸዉ ተገለጸ

ማህበራት በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ፣ አገራዊ አመለካከት ፣ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ መፍጠር እንዳለባቸዉ ተመለከተ›፡፡
የኢትጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት መምህራን ፣ሴቶች እና ወጣቶች ማህበራት አመራሮች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 1/2007 ዓ.ም በሀዋሳ ፒና ሆቴል ባዘጋጀዉ የመራጮች እና ስነ ዜጋ ስልጠና ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሚኒስትር ማዕረግ የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንደገለጹት የብዙሃን ማህበራት ለዴሞክራሲ ግንባታ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል፡፡
የስነ ዜጋ ትምህርት የዴሞክራሲ ህልዉና እንዲጠበቅ ፣ስርአቱ እንዲያብብ ህዝቡ የስልጣን ባለቤትነቱን እንዲያረጋግጥና በህዝብ የተመረጠ መንግስት እዉን ለማድረግ ጠቀሜታ እንዳለዉ ተገንዝበናል ያሉት ፕሮፌሰር መርጋ ስልጠናዉ ስለዴሞክራሲያዊ ስርአት ፣ስለህዝብ ስልጣን ባለቤትነት ስለሰብአዊና ዴሞክራሲዊ መብቶቻቸዉ ግንዛቤና እዉቀት የሚያዳብሩበት ነዉ ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰር መርጋ ጨምረዉም የመራጮችና ስነ ዜጋ ትምህርት ዋና ዓላማ ዜጎች ተገቢዉን እዉቀትና ግንዛቤ አግኝተዉ በሃገሪቱ በሚካሄዱ የልማት ተግባራት ንቁ ተሳታፊ አንዲሆኑ ነዉ ብለዉ ማህበራትም ለዴሞክራሲዊ ስርአት ግንባታ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻልም ቦርዱ እየሰራበት ያለ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ቦርዱ በእዉቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ እንዲካሄድና እስካሁን ከተካሄዱት ምርጫዎች በተሻለ ደረጃ ቀጣዩን ምርጫ ለማስፈጸም ጠንክሮ እሰራ ይገኛል ያሉት ፕሮፌሰር መርጋ ካላቸዉ ተደራሽነት አንጻር እስከታችኛዉ የህብረተሰብ ክፍል ይህንኑ የስነዜጋ ትምህርት ያወርዳሉ ተብለዉ ከሚታመንባቸዉ ማህበራት ጋር ለአንድ ኣመት ያህል ሲሰራ እንደመጣ ነዉ ያስረዱት፡፡
በ2006 ዓ.ም ለስምንቱ ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ትምህርቱ እንደተሰጠ ያወሱት የቦርዱ ሰብሳቢበክልሉ እየተሰጠ ያለዉ ስልጠናም የዚሁ እቅድ አንድ አካል መሆኑን አስረድተዉ ማህበራቱ የ ስነ ዜጋ ትምህርት ለዜጎች በማድረስ ረገድ ለሚያከናዉኗቸዉ ተግባራት የቦርዱ ድጋፍ እንደማይለያቸዉ ገልጸዋል፡፡

 

 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ