ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና በመራጮች ህጎችና ስነ ዜጋ ትምህርት ላይ ውይይት ተካሄደ
     
 
Banner

በመራጮች ህጎችና ስነ ዜጋ ትምህርት ላይ ውይይት ተካሄደ PDF Print E-mail

በመራጮች ህጎችና ስነ ዜጋ ትምህርት ላይ ውይይት ተካሄደ

ሀገሪቱ የጀመረችው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በአስተማማኝ መሰረት ላይ እንዲገነባ የመምህራን፣ ሴቶችና ወጣቶች ማህበራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ።

ለኦሮሚያ ክልል መምህራን፣ሴቶችና ወጣቶች ማህበራት በምርጫ ህግ፣ በመራጮችና ስነ ዜጋ ትምህርት ላይ በተዘጋጀ የምክከር መድረክ ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጊያ በቃና እንደገለፁት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲጎለብት በየደረጃው የሚገኙ ስቪል ማህበራት አደረጃጀቶች ወሳኝ ድርሻ አላቸው።

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በተካሔደው አራት ጠቅላላ ብሔራዊ ምርጫ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ስልጣን ላይ እንዲወጣ ዜጎች በህገ መንግስቱ፣በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና በህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲያገኙ መደረጉን ገልጠዋል።

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የመምህራን፣የሴቶችና ወጣቶች ማህበራት አመራሮች በመራጮች ህጎችና ደንቦች፣በስነ ዜጋና ስነ ምግባር ደንቦች ላይ በቂ ግንዛቤና ዕውቀት ይዘው ለአባሎቻቸው እንዲያካፍሉ ለማድረግ ነው ብለዋል።

የህዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነትን በማረጋገጥ በኩል የስቪል ማህበራት የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑን ፕሮፈሰር መርጊያ በቃና አሳስበዋል።

በያዝነው አመት የሚካሄደው አምስተኛው ምርጫ በዕውቀት ላይ የተመሰረተና ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና የህዝብ አመኔታ ያተረፈ ምርጫ እንዲሆን ቦርዱ በቂ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጠዋል።

ቦርዱ በቅድመ ምርጫ ምዕራፍ ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ መስተዳድር የመምህራን፣ ሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች ጋር በቅድመ ምርጫ ምዕራፍ ላይ በጋራ እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በአዳማ ከተማ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የመራጮችና ስነ ዜጋ ትምህርት የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ ላይ ከኦሮሚያ 18 ዞኖችና የከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ የመምህራን ፣ሴቶችና ወጣቶች ማህበራት አመራሮችና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

 

 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ