ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ
     
 
Banner

የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ PDF Print E-mail

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ አጥቷል። በዚህም መሰረት በዋናነት የሚጠበቁት ክንውኖች በሚከተለው ጊዜ ይፈጸማሉ:-

በምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገኝተው የመወዳደሪያ  ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት፤ ከህዳር 15 እስከ 30 2007 ዓ.

· የምርጫ ክልሎች ጽ/ቤቶች ተከፍተው ሥራቸውን በይፋ የሚጀምሩት ታህሳስ 1 ቀን 2007 ዓ.ም

· መራጩ ሕዝብ በየምርጫ ጣቢያው በይፋ በሚደረግለት ጥሪ መሰረት በሚካሄደው የአንድ ቀን ስብሰባ የምርጫ ጣቢያ የሕዝብ ተዛቢዎችን የሚመረጥበት፤ ታህሳስ 12 ቀን 2007 ዓ.ም

· የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች ምዝገባ በየምርጫ ክልሉ ጽ/ቤት የሚካሄድበት፤ ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 27 ቀን 2007 ዓ.ም

· የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው ሥራቸውን በይፋ የሚጀምሩበት፤ ታህሣስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም

· የመራጮች ምዝገባ በየምርጫ ጣቢያው የሚካሄድበት፤ ከጥር 1 እስከ የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም

· የመራጮች መዝገብ በየምርጫ ጣቢያው ለሕዝብ ይፋ ሆኖ የሚቆይበት፤ ከየካቲት 15 እስከ 19 ቀን 2007 ዓ.ም

· የዕጩዎች ዝርዝር ለየምርጫ ክልሉ ሕዝብ ይፋ የሚደረግበት፤ የካቲት 1 ቀን 2007 ዓ.ም

· የዕጩነት ማረጋገጫ መታወቂያ ካርድ የሚስጥበት ከየካቲት 2 እስከ 7 ቀን 2007 ዓ.ም

· የዕጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ በይፋ የሚጀመርበት፤ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም

· የዕጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ በይፋ የሚጠናቀቅበት ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ስዓት

· የድምጽ መስጫ ዕለት ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት

· የድምጽ ቆጠራ ወዲያውኑ በየምርጫ ጣቢያው የሚከናወንበት፤ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ

· የድምጽ ቆጠራ ውጤት ለየምርጫ ጣቢያው ለሕዝብ በማስታወቂያ ሰሌዳ በይፋ የሚገለጽበት፤ ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ.ም

· በየምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ ውጤት በሚገኙበት የምርጫ ክልል ጽ/ቤት የሚደመርበትና ውጤቱ በማስታወቂያ ሰሌዳ ለሕዝብ በይፋ የሚገለጽበ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም

· የምርጫው አጠቃላይ ውጤት በብሔራዊ ደረጃ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሚጸድቅበትና ውጤቱ በይፋ ለሕዝብ የሚገለጽበት ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ይሆናል።

ከህዳር 15 እስከ 30 2007 ዓ.ም በምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገኝተው የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን መርጠው መውሰዳቸውንና የምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች ታህሳስ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ተከፍተው ሥራቸው በይፋ መጀመራቸውን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

 

 

 

 

 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ