ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና በዓሉ ቦርዱ የተጣለበትን ህገ መንግሥታዊ አደራ በላቀ ተነሳሽነት እንዲፈጽም የሚያስችለዉ መሆኑ ተገለጸ
     
 
Banner

በዓሉ ቦርዱ የተጣለበትን ህገ መንግሥታዊ አደራ በላቀ ተነሳሽነት እንዲፈጽም የሚያስችለዉ መሆኑ ተገለጸ PDF Print E-mail
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 5ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ የሚገኝበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ተልኮችንን በትጋት እንድንወጣ እና የተጣለብንን ህገ መንግሥታዊ አደራ በላቀ ተነሳሽነት እንድንፈጽም ስንቅ ይሆነናል ሲሉ የቦርዱ ም/ሰብሳቢ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮችና ሰራተኞች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በማስመልከት ባደረጉት ዝግጅት ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉትና ዉይይቱን የመሩት የቦርዱ ም/ሰብሳቢ ዶ.ር አዲሱ ገ/እዚአብሔር ህገ መንግሥታችን የጸደቀበት 2ዐኛ ዓመት እየተከበረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 5ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ የሚገኝ በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ተልኮችንን በትጋት እንድንወጣ እና የተጣለብንን ህገ መንግሥታዊ አደራ በላቀ ተነሳሽነት እንፈጽም ዘንድ ስንቅ ይሆነናል ብለዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ የሕዝቦቿን ጥቅም የሚያረጋግጥ ህገ መንግሥታዊ ስርዓት ለመመስረት በሕዝቦቿ ፈቃድና ፍላጎት ህገ መንግሥት አፅድቃ መንቀሳቀስ ከጀመረች 2ዐ ዓመታት እንተቆጠሩ ያወሱት ዶ.ር አዲሱ
አገራችንና ሕዝቦቿ በነዚህ ሃያ ዓመታት በርካታ ለውጦችን እንዳዩና ለዓለም የሚተርፍ የህገ መንግሥታዊ ስርዓት ግንባታ ልምድ እንዳበረከቱ ገልጸዋል፡፡
ቦርዱ ምርጫን በገለልተኝነት ለማስፈፀም የተቋቁመ ተቋም እንደመሆኑ የተጣለበትን ህገ መንግሥታዊ አደራ ለመወጣት በቁርጠኝነት እያገለገለ መሆኑን የጠቀሱት ዶ.ር አዲሱ ቦርዱ በሰው ሃይል አደረጃጀት፣በመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥና በቁሳቁስ ዝግጅት ረገድ ወሳኝ ሥራዎችን ያከናወነ ከመሆኑም ባሻገር ምርጫው ካለ እንከን እንዲከናወን አለማቀፍ ተሞክሮችን ቀምሯል ብለዋል፡፡
ዶ.ር አዲሱ አክለዉም ሕዝቦች ፈቃዳቸውን በሰጡት ብቻ እንዲመሩ ሕገ መንግሥቱ ሙሉዕነት ያለው መብት አጎናጽፉቸዋል ብለዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ሕዝቦች ይኸው መብት ሳይሸራረፍ እንዲጠቀሙበት እስካሁን ድረስ በአገራችን በካሄዳቸው አራት ጠቅላላ ምርጫዎች አፈፃፀሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ በመምጣት ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ያደረገ ቢሆንም 5ኛው ጠቅላላ ምርጫ ደግሞ በላቀ ትጋትና ወኔ እንድንወጣ ይህ በዓል ቃል የምንገባበት ነው ነዉ ሲሉ ነዉ የገለጹት፡፡
ሀገራችን የጀመረችውን የልማት እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አጠናክሮ ለመቀጠል ቦርዱ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ም/ሰብሳቢዉ ከነዚህ አንዱ ምርጫው እንከን እንዳይገኝበት ጠንክሮ መስራት በመሆኑ የቦርዱ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት የምርጫውን ሂደት በጥንቃቄ መምራት መቼም ሊዘነጉት የሚገባ እንዳልሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል ፡፡
የቦርዱ ሰራተኞች በበኩላቸዉ እስካሁን ድረስ ያለዉን የቁሳቁስ ዝግጅት፣ስርጭት፣ስልጠና መስጠትና መሰል ለሂደቱ አጋዥ የሆኑ ክንዉኖችን ከተያዘለት ጊዜ ቀድመዉ ማጠናቀቃቸዉን ገልጸዉ ቀጣይ ስራዎችንም በላቀ ትጋትና ጥንቃቄ እንደሚያከናዉኑ ቃል ገብተዋል፡፡
 

 

ክልላዊ መረጃ

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ