ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የስነምግባር እና የአሰራር መመሪያ ረቂቅ አዘጋጀ
     
 
Banner

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የስነምግባር እና የአሰራር መመሪያ ረቂቅ አዘጋጀ PDF Print E-mail

የካቲት 1 ቀን 2002

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መመሪያ ረቂቅ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጫ ህጋዊነት የሚረጋገጠው በሃገሪቱ ተቋማት ህግ እንዲሁም በሃገሪቱ ህዝብ መሆኑን ይገለፃል። በምርጫ ሂደት ውስጥ የታዛቢዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያትታል። አለም አቀፍ ታዛቢዎችም የምርጫው ሂደት በገለልተኝነት እና ተዓማኒነት ባለው መንገድ በመታዘብ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱም ይገልፃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የስነምግባር መመሪያ ረቂቅ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እና ከምርጫ 97 የተገኙ ልምዶችን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት አለም አቀፍ ታዛቢዎች በመንግስት ጋባዥነት ሲመጡ የሃገሪቱ ህግና ሉዓላዊነት እንዲሁም የምርጫ ቦርድ ሕግን በማክበር እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል የስነ ምግባር መመሪያው መዘጋጀቱ ወሳኝ ነው። በመመሪያው ረቂቅ ላይ ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች በማን እንደሚጋበዙ፣ ስራቸውን በምን ሁኔታ እንደሚያካሂዱ በስራቸው ወቅት ሊከተሉዋቸው ስለሚገባ ሕጎች፣ የምርጫውን ሂደት በተመለከተ በምን ሁኔታ አስተያየት እንደሚሰጡ እና ሌሎች መመሪያዎችን ያካተቱ ነው።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ስነ ምግባር እና የአሰራር መመሪያ ዙርያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ቦርዱ ሰፊ ውይይት አካሂዷል። በመመሪያው ላይ በቀረቡት ሃሳቦች ላይ ውይይት በማድረግ እና የቀረቡት ሃሳቦችን እንደሚያስተናግድ ነው ቦርዱ ያስታወቀው።

 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ