ቌንቌ | Language
     
 
መግቢያ ዜና በመላው አገሪቱ 24 ሚሊዮን 931 ሺህ በላይ ሕዝብ የመራጭነት ካርድ ወስዷል
     
 
Banner

በመላው አገሪቱ 24 ሚሊዮን 931 ሺህ በላይ ሕዝብ የመራጭነት ካርድ ወስዷል PDF Print E-mail

የካቲት 2 ቀን 2002

በመጪው ግንቦት በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በመላው አገሪቱ የመራጮች ምዝገባ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ስምንት ቀናት ብቻ ቀርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ አሰፋ እንደገለጹት እስከ ጥር 30 ቀን 2002 ድረስ ብቻ በመላው አገሪቱ 24ሚሊዮን 931 ሺህ በላይ ሕዝብ የመራጭነት ካርድ ወስዷል፡፡

በአጠቃላይ በአገሪቱ በምርጫው ይሳተፋል ተብሎ ከሚገመተው ሕዝብ በላይ እየተመዘገበ በመሆኑ ቦርዱ ተጨማሪ ሁለት ሚሊዮን የድምጽ መስጫ ካርዶችን ለማሰራጨት ተገዷል፡፡ እስካሁን 45 የፖለቲካ ፓርቲዎች በእጩዎች ምዝገባ ሂደት በመሳተፍ ላይ እንደሆነ የገለጹት ዋና ኃላፊው፣ ፓርቲዎቹ 1ሺህ 401 እጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2 ሺህ 952 ዕጩዎችን ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች አስመዝገበዋል፡፡

ሁሉም ፓርቲዎች ለሕዝብ ተወካዮች ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ናቸው፡፡ አቶ ኤርሚያስ እንደተናገሩት 36 የግል እጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ተመዝግበዋል፡፡ እንዲሁም 10 ያህል የግል ተወዳዳሪዎች ደግሞ በክልል ምክር ቤቶች በሚካሄዱ ውድድሮች ለመሳተፍ ተመዝግበዋል፡፡

በኦሮሚያ፣በደቡብና በአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ቁጥር ከተጠበቀው በላይ እየሆነ በመምጣቱ ቦርዱ የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ተከታትሎ ሌላ የምርጫ ጣቢያ በመክፈት ኅብረተሰቡን ለማስተናገድ የሚያስችል አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሆነ ዋና ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የመራጮች ምዝገባ ቀን ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት ጊዜ ብቻ መቅረቱን ያስታወሱት ዋና ኃላፊው፣ መላው ሕዝብ ሕገ መንግሥታዊ መብቱን ለመጠቀም ለመራጭነት የሚያበቃውን ካርድ በጊዜው እንዲወስድም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በግንቦት ወር በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ 32 ሚልየን ሕዝብ በመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቦርዱ አስታውቋል።


 

 

አዳዲስ ዝግጅቶች

ለጊዜው ምንም ዝግጅት አልተገኘም
 


ኮፒራይት © 2010
የኢትዮጵያ ብሔራዌ ምርጫ ቦርድ