National Electoral Board of Ethiopia (NEBE) 5th General Election — 2010 E.C.

እንኳን ወደ ምርጫ ቦርዱ ድህረገፅ ደህና መጡ

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ። በ2002 ዓ.ም የተካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ ውጤቶች፣ ደንቦችና መረጃዎች ያገኛሉ።

ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በመላው ሀገሪቱ የተካሄደው አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ውጤት


በ2002 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ዕጩዎች ያገኙት ጠቅላላ ድምፅ


በ2002 ዓ.ም በተካሄደው አገር አቀፍ የክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫ ዕጩዎች ያገኙት ጠቅላላ ድምፅ


በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ

ፀድቆ ይፋ የተደረገ ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የተካሄደው

ጠቅላላ ምርጫ ውጤት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በመላው ሀገሪቱ አራተኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ ለማስፈፀም ባወጣው የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ምርጫው የተረጋጋ፣ ቀልጣፋ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና የሕዝብ አመኔታ በተረጋገጠበት መልኩ ተጠናቋል፡፡

የምርጫው አጠቃላይ ውጤት ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በቦርዱ ፀድቆ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ቀድሞ በወጣው የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሠሌዳ ተገልጿል፡፡

በተሻሻለው የምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም አንቀፅ 76 ንዑስ አንቀፅ 5 መሠረት ቦርዱ በአጠቃላይ የምርጫው ውጤት ከየምርጫ ክልሉ ተጠናቆ እስከሚደርሰው ድረስ ከግንቦት 16 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ጀምሮ ከየምርጫ ክልሉ የመጣለትን፣

  1. የ547 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት፣
  2. የ9ኙን ክልሎች የክልል ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት፣

ግንቦት 16፣ 17 እና 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በቦርዱ ጽሕፈት ቤት ለሀገር ውስጥና ለውጪ የመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል፡፡

ቦርዱ ሰኔ 11 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ባካሄደው 149ኛ አስቸኳይ ስብሰባው፣

- ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በመላው ሀገሪቱ የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ከየምርጫ ክልሉ ተጠቃሎ ለቦርዱ መድረሱን፣

- በአሁኑ ጊዜ ህጉን ተከትሎ ለቦርዱ ቀርቦ ውሣኔ ያላገኘ አቤቱታ አለመኖሩን በማረጋገጥና ውጤቱን በጥልቀት መርምሮ በማፅደቅ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ወስኗል፡፡

በመሆኑም ግንቦት 15 ቀን በመላው ሀገሪቱ የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1ኛ/ በምርጫው 63 የፖለቲካ ድርጅቶች ተሳትፈው

1.1 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ወንድ 1,916 (87.6%) ሴት 272 (12.4%)

በጠቅላላም 2,188 ዕጩዎችን፣

1.2 ለክልል ምክር ቤት ምርጫ ወንድ 4,ዐ21(84.7%) ሴት 725 ( 15.3%)

በጠቅላላው 4,746 ዕጩዎችን

1.3 በግል

  • ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ወንድ 33 (97.1%) ሴት 1(2.9%) በጠቅላላው 34 ዕጩዎችን
  • ለክልል ምክር ቤት ምርጫ ወንድ 9 (81.8%) ሴት 2 (18.1%) በጠቅላላ 11 ዕጩዎችን፣ በጠቅላላው ወንድ 5,979 (85.7%) ሴት 1,ዐዐዐ (14.3%) በጠቅላላው 6,979 ዕጩዎች በማቅረብ ተወዳድረዋል፡፡

2ኛ/ ለመምረጥ የተመዘገበው ሕዝብ ወንድ 16,674,280 (52.2%) ሴት 15,252,24ዐ (47.8%) በድምሩ 31,926,52ዐ ነው፡፡

3ኛ/ ድምፅ የሰጠው ሕዝብ ወንድ 15,617,453 (52.4%) ሴት 14,214,737 (47.6%) በድምሩ 29,832,19ዐ ነው፡፡

4ኛ/ ከተመዘገበው ውስጥ ድምፅ የሰጠ መራጭ 93.4 በመቶ ነው፡፡ ከተመዘገበው ውስጥ ድምፅ ያልሰጠው መራጭ 6.6 በመቶ ነው፡፡

1. የጠቅላላ ምርጫ ውጤት

1.1 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ ውጤት

በጠቅላላው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ከተካሄደባቸው 547 የምርጫ ክልሎች ውስጥ፣

  • የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 499 መቀመጫዎች፣
  • የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) 8 መቀመጫዎች፣
  • የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶሕዴፓ) 24 መቀመጫዎች፣
  • የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉሕዴፓ) 9 መቀመጫዎች፣
  • የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህአዴን) 3 መቀመጫዎች፣
  • የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) 1 መቀመጫ፣
  • የአርጎባ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ) 1 መቀመጫ፣
  • የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) 1 መቀመጫ፣
  • በግል 1 መቀመጫ፣

አሸንፈዋል፡፡

2. የክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫ ውጤት

በመላው ሀገሪቱ በ9 ክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ተካሂዷል፡፡ ውጤቱም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2.1 ትግራይ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት 152 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት-ኢህአዴግ) 152 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡

2.2. አፋር

የአፋር ክልል ምክር ቤት 96 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) 93 መቀመጫዎች፣
  • የአርጎባ ህዝብ ዴምክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ) 3 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡

2.3. አማራ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 294 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን-ኢህአዴግ) 294 መቀመጫዎች አሸንፏል

2.4. ኦሮሚያ

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት 537 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ-ኢህአዴግ) 537 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡

2.5. ሶማሌ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 186 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ሶህዴፓ) 186 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡

2.6 ቤንሻንጉል ጉሙዝ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 99 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉሕዴፓ) 98 መቀመጫዎች፣
  • የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) 1 መቀመጫ አሸንፏል፡፡

2.7. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች

  • የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 348 መቀመጫዎች አለው፡፡
  • የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን-ኢህአዴግ) 348 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡

2.8. የጋምቤላ ሕዝቦች

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 156 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) 156 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡

2.9. የሐረሪ ሕዝብ

የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት 36 መቀመጫዎች አለው፡፡

  • የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) 18 መቀመጫዎች፣
  • የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞከራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ-ኢህአዴግ) 18 መቀመጫዎች አሸንፈዋል፡፡

3. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች የአሸናፊ የፖለቲካ ድርጅቶችና ዕጩዎች ዝርዝርና ያገኙት ድምፅ በቦርዱ ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቦርዱ ጥቅምት 24 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ባወጣው የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ለሕዝብ እነሆ ይፋ ተደርጓል፡፡ ይኸው ዝርዝር በተከታታይ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ይወጣል፡፡ በተጨማሪም በቦርዱ ድህረ ገፅ ዛሬ ተጭኗል፡፡

4. በተመሳሳይ ሁኔታ ለጠቅላላ ምርጫ በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል የተወዳደሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩዎች ያገኙት ድምፅ ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

II. ግንቦት 22 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በሶማሌ ክልል የተካሄደው የአካባቢ ምርጫ ውጤት

ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የካቲት 24 ቀን በ2ዐዐ2 ዓ.ም. ባወጣው የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በሶማሌ ክልል ግንቦት 22 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የአካባቢ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሀዊ፣ ሠላማዊ ዴሞክራሲያዊና የሕዝብ አመኔታን ባተረፈ መልኩ መከናወኑን አረጋግጧል፡፡

በዚሁ መሠረት ቦርዱ በክልሉ የተካሄደውን የአካባቢ ምርጫ ውጤት መርምሮ እና አፅድቆ ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ይፋ እንዲሆን በወሰነው መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው እንገልፃለን፡፡

1. የጅጅጋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ምርጫ ውጤት

  • የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) በ13 ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙትን 75 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡ ከዚህ ውስጥ ወንድ 51 (68%) ሴት 24 (32%) ናቸው፡፡

2. የወረዳ ምክር ቤት አባላት ምርጫ ውጤት

  • የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) በ52ቱም ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙትን 4,032 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡ ከዚህ ውስጥ ወንድ 3,412 (84.6%) ሴት 620 (15.4%) ናቸው፡፡

3. የቀበሌ ምክር ቤት አባላት ምርጫ ውጤት

  • የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) በ7ዐ6 ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙትን 47,849 መቀመጫዎች አሸንፏል፡፡ ከዚህ ውስጥ ወንድ 37,541 (78.5%) ሴት 10,308 (21.5%) ናቸው፡፡

የሶማሌ ክልል የአካባቢ ምርጫ ውጤት ዝርዝርም በቦርዱ ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ይፋ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፀደቀ

ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በመላው ሀገሪቱ የተካሄደው አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ

የክልል ምክር ቤቶች አጠቃላይ ውጤት

ዘጠኝ ክልሎች በድምሩ 1,9ዐ4 የክልል ምክር ቤቶች መቀመጫዎች አላቸው፡፡

ተ.ቁ.

ክልል

የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት

አሸናፊ ፓርቲ

ያገኙት መቀመጫ

1

ትግራይ

152

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ሕወሓት - ኢሕአዴግ/

152

2

አፋር

96

የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/

93

የአርጎባ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /አሕዴድ/

3

3

አማራ

294

ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን - ኢሕአዴግ/

294

4

ኦሮሚያ

537

የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦሕዴድ - ኢሕአዴግ/

537

5

ሶማሌ

186

የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሶሕዴፓ/

186

6

ቤንሻንጉል ጉሙዝ

99

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ቤጉሕዴፓ/

98

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/

1

7

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች

348

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢሕዴን - ኢሕአዴግ/

348

8

ጋምቤላ

156

የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋሕአዴን/

156

9

ሐረሪ

36

የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ /ሐብሊ/

18

የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦሕዴድ - ኢሕአዴግ/

18

ያሸነፉት መቀመጫ ብዛት ድምር

1,9ዐ4

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፀደቀ

ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በመላው ሀገሪቱ የተካሄደው አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጠቃላይ ውጤት

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 547 መቀመጫዎች አሉት፡፡

ተ.ቁ.

አሸናፊ ፓርቲ

ያገኙት መቀመጫ

1

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/

499

2

የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሶሕዴፓ/

24

3

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ቤጉሕዴፓ/

9

4

የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/

8

5

የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋሕአዴን/

3

6

የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ /ሐብሊ/

1

7

የአርጎባ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /አሕዴድ/

1

8

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ /መድረክ/

1

9

በግል

1

ያሸነፉት መቀመጫ ብዛት ድምር

547

 

Latest Election News

Election 2021
Jun 22, 2021
Prosperity Party Wins Landslide Victory in 2021 Election
PP secured 457 of 547 seats in the House of Peoples' Representatives, delivering a commanding majority.
Read more →
Jun 23, 2021
Over 38 Million Voters Participate in 6th General Election
Millions exercised their democratic right across 50,000+ polling stations in a largely peaceful election.
Read more →
Jun 24, 2021
African Union Observers Assess Ethiopia's 2021 Election
The AU-EOM noted improvements in electoral administration while highlighting ongoing security challenges.
Read more →
Oct 4, 2021
Abiy Ahmed Confirmed as Prime Minister for Second Term
Parliament officially confirmed PM Abiy Ahmed for a new five-year term following the PP's election victory.
Read more →
Election 2026
Jan 15, 2026
Ethiopia Sets June 1, 2026 as Date for 7th General Election
NEBE officially announced June 1 as election day, with 47 registered parties set to compete.
Read more →
Mar 10, 2026
Over 10,900 Candidates Register for the 7th General Election
47 parties fielded 10,934 candidates including 2,098 for the House of Peoples' Representatives.
Read more →
Apr 9, 2026
More Than 42 Million Citizens Register to Vote in 2026
Voters registered via in-person centres and the new Mirchaye mobile app in a nationwide campaign.
Read more →
Apr 12, 2026
NEBE Finalizes Preparations for Nationwide Vote
52,720 polling stations designated, security classification system deployed across all regions.
Read more →